በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በጴንጤቆስጤ በዓል ላይ የተከናወነ ተአምር!

በጴንጤቆስጤ በዓል ላይ የተከናወነ ተአምር!

ለወጣት አንባቢያን

በጴንጤቆስጤ በዓል ላይ የተከናወነ ተአምር!

መመሪያ፦ ይህን መልመጃ ጸጥታ በሰፈነበት ቦታ ሆነህ ሥራ። ጥቅሶቹን ስታነብ በቦታው እንዳለህ አድርገህ አስብ። ሁኔታውን በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል እንዲሁም በታሪኩ ውስጥ የተጠቀሱት ሰዎች ሲነጋገሩ ድምፃቸውን ለመስማትና ስሜታቸውን ለመረዳት ሞክር። ታሪኩ ሕያው እንዲሆንልህ አድርግ።

ሁኔታውን ለማስተዋል ሞክር።የሐዋርያት ሥራ 2:1-21, 38-41ን አንብብ።

ስለ ‘ኃይለኛው ነፋስ’ እንዲሁም ‘የእሳት ነበልባል ስለሚመስሉት ምላሶች’ የሚናገረውን ዘገባ ስታነብ ወደ አእምሮህ የሚመጣው ምንድን ነው?

․․․․․

ደቀ መዛሙርቱ በውጭ አገር ቋንቋ ሲናገሩ የሰሙት ሰዎች ምን ያሉ ይመስልሃል?

․․․․․

በቁጥር 13 ላይ በተጠቀሱት ፌዘኛ ሰዎች ፊት ላይ ምን ዓይነት ስሜት ይነበብ እንደነበር ለመገመት ሞክር።

․․․․․

ጥልቅ ምርምር አድርግ

ጴንጤቆስጤ ምን ዓይነት በዓል ነበር? ይህ በዓል በኢየሩሳሌም በተሰበሰቡት ሰዎች ላይ ምን ስሜት ፈጥሯል? (ዘዳግም 16:10-12)

․․․․․

ጴጥሮስ በዚያ ለተሰበሰቡት ሰዎች ሲናገር ለአድማጮቹ አክብሮት እንዳለው ያሳየው እንዴት ነው? እንዲሁም በጋራ የሚያስማማቸውን ሐሳብ የመረጠውስ እንዴት ነው? (የሐዋርያት ሥራ 2:29)

․․․․․

ጴጥሮስ በጴንጤቆስጤ በዓል ላይ ያሳየው ድፍረት በሊቀ ካህናቱ ግቢ ካሳየው ባሕርይ ፍጹም የተለየ የሆነው እንዴት ነው? (ማቴዎስ 26:69-75)

․․․․․

ከዚህ ታሪክ ያገኘኸውን ትምህርት ተግባራዊ አድርግ። ከዚህ በታች ስለተዘረዘሩት ነገሮች ምን ትምህርት እንዳገኘህ ጻፍ፦

በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተውን ትምህርት ለሌሎች በምናካፍልበት ጊዜ በጋራ የሚያስማሙንን ሐሳቦች የመምረጥንና በአክብሮት የመናገርን አስፈላጊነት በተመለከተ ያገኘኸውን ጥቅም ጻፍ።

․․․․․

በአሁን ጊዜ የምታፍር ወይም የምትፈራ ብትሆንም እንኳ ወደፊት ደፋር የይሖዋ አገልጋይ ስለ መሆን ያገኘኸውን ትምህርት ጻፍ።

․․․․․

ከዚህ ታሪክ ውስጥ ልብህን ይበልጥ የነካው ምንድን ነው? ለምንስ?

․․․․․

ተጨማሪ ምርምር ለማድረግ የመስከረም 15, 1996 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 8 እና 9⁠ን ተመልከት።