በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ትሑትና ደፋር የነበረ ሰው

ትሑትና ደፋር የነበረ ሰው

ለታዳጊ ወጣቶች

ትሑትና ደፋር የነበረ ሰው

ዮናስ—ክፍል 1

መመሪያ፦ ይህን መልመጃ ጸጥታ በሰፈነበት ቦታ ሆነህ ሥራ። ጥቅሶቹን ስታነብ በቦታው እንዳለህ አድርገህ አስብ። ሁኔታውን በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል እንዲሁም በታሪኩ ውስጥ የተጠቀሱት ሰዎች ሲነጋገሩ ድምፃቸውን ለመስማትና ስሜታቸውን ለመረዳት ሞክር። ታሪኩ ሕያው እንዲሆንልህ አድርግ።

1 ሁኔታውን ለማስተዋል ሞክር።ዮናስ 1:1-17 እንዲሁም ከ2:10 እስከ 3:5 ድረስ አንብብ።

ማዕበሉ ምን ዓይነት ድምፅ የነበረው ይመስልሃል? ማዕበሉ ሲታይ ምን ይመስል ነበር?

․․․․․

ዮናስና በመርከቧ ላይ የነበሩት ሰዎች ድምፅ ምን ዓይነት ስሜት እንደነበራቸው የሚንጸባረቅበት ይመስልሃል?

․․․․․

ዮናስ በባሕሩ ውስጥ በሰመጠበት ጊዜ እንዲሁም ትልቁ ዓሣ ከዋጠው በኋላ ምን አስቦ ሊሆን እንደሚችል ግለጽ። (ዮናስ 2:1-9⁠ን አንብብ።)

․․․․․

2 ጥልቅ ምርምር አድርግ።

በነነዌ ምን ዓይነት ሰዎች ይኖሩ ነበር? ዮናስ መጀመሪያ ላይ ወደ እነሱ ለመሄድ የፈራው ለምን ሊሆን ይችላል? (ናሆም 3:1)

․․․․․

ነነዌ በአምላክ ዘንድ “ታላቅ ከተማ” ነበረች ሲባል ምን ማለት ነው? (ዮናስ 3:3፤ 2 ጴጥሮስ 3:9)

․․․․․

ዮናስ ስለ ሠራው ስህተትም ሆነ ስለ አምላኩ ሲናገር ግልጽ መሆኑ ስለ እሱ ምን ይጠቁማል? (ዮናስ 1:9, 10ን በድጋሚ አንብብ።)

․․․․․

ዮናስ ወደ ባሕሩ ከተጣለ በኋላ በመርከቧ ላይ የነበሩት ሰዎች ስላደረጉት ነገር ያወቀው እንዴት ሊሆን ይችላል? (ዮናስ 1:15, 16ን በድጋሚ አንብብ።)

․․․․․

3 ከዚህ ታሪክ ያገኘኸውን ትምህርት ተግባራዊ አድርግ። ከዚህ በታች ስለተዘረዘሩት ነገሮች ምን ትምህርት እንዳገኘህ ጻፍ፦

ስለ ፍርሃት።

․․․․․

ስለ ትሕትና።

․․․․․

ስለ ድፍረት።

․․․․․

ይሖዋ ስለ ሰዎች ሌላው ቀርቶ እኛ ክፉዎች እንደሆኑ አድርገን ስለምናስባቸው ሰዎች ጭምር ስላለው አመለካከት ምን ተምረሃል?

․․․․․

4 ከዚህ ታሪክ ውስጥ ይበልጥ ትምህርት ያገኘህበት ሐሳብ የትኛው ነው? ለምን እንዲህ አልክ?

․․․․․

ተጨማሪ ምርምር ለማድረግ የጥር 1, 2009 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 25-28 ተመልከት።

በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ሌሎች ጽሑፎች ለማግኘት www.watchtower.org ተመልከት።