በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

እውነተኛ ሰላምና ደኅንነት የሚገኘው መቼ ነው?

እውነተኛ ሰላምና ደኅንነት የሚገኘው መቼ ነው?

ልዩ የሕዝብ ንግግር

እውነተኛ ሰላምና ደኅንነት የሚገኘው መቼ ነው?

ለበርካታ መቶ ዓመታት የሰው ልጆች ሰላምና ደኅንነት ለማግኘት ጥረዋል። ይሁንና እውነተኛ ሰላምና ደኅንነት ማግኘት አስቸጋሪ ሆኖባቸዋል። ለምን? መጽሐፍ ቅዱስ ሰላም ማግኘት አስቸጋሪ እንዲሆን ያደረጉትን ሁለት መሠረታዊ ምክንያቶች ይገልጻል። ከዚህም በተጨማሪ አምላክ፣ ለሰው ዘሮች እውነተኛ ብሎም ዘላቂ የሆነ ሰላምና ደኅንነት በዓለም ዙሪያ እንደሚያመጣ የሚገልጽ አስደሳች ተስፋ ይዟል።

እንዲህ ያለው ሰላምና ደኅንነት እውን የሚሆነው መቼና እንዴት ነው? እንዲህ ባለው አስደሳች ሁኔታ ውስጥ ለመኖር ምን ማድረግ ይኖርብሃል? “እውነተኛ ሰላምና ደኅንነት የሚገኘው መቼ ነው?” የሚለው የሕዝብ ንግግር ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል። በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተው ይህ ንግግር፣ በመላው ዓለም ከ230 በሚበልጡ አገሮች ይሰጣል። በአብዛኞቹ ቦታዎች ንግግሩ የሚቀርበው እሁድ፣ ሚያዝያ 18, 2010 (እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር ሚያዝያ 10, 2002) በይሖዋ ምሥክሮች የመንግሥት አዳራሽ ነው። በአካባቢህ ያሉት የይሖዋ ምሥክሮች ንግግሩ የሚቀርብበትን ሰዓትና ቦታ ሊነግሩህ ፈቃደኞች ናቸው። በዚህ ስብሰባ ላይ እንድትገኝ ሞቅ ያለ ግብዣ እናቀርብልሃለን።