በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ለምታምንበት ነገር የጸና እምነት ይኑርህ!

ለምታምንበት ነገር የጸና እምነት ይኑርህ!

ለታዳጊ ወጣቶች

ለምታምንበት ነገር የጸና እምነት ይኑርህ!

መመሪያ፦ ይህን መልመጃ ጸጥታ በሰፈነበት ቦታ ሆነህ ሥራ። ጥቅሶቹን ስታነብ በቦታው እንዳለህ አድርገህ አስብ። ሁኔታውን በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል እንዲሁም በታሪኩ ውስጥ የተጠቀሱት ሰዎች ሲነጋገሩ ድምፃቸውን ለመስማትና ስሜታቸውን ለመረዳት ሞክር። ታሪኩ ሕያው እንዲሆንልህ አድርግ።

ዋነኞቹ ባለ ታሪኮች፦ ኤርምያስ፣ አቤሜሌክና ንጉሥ ሴዴቅያስ

ታሪኩ በአጭሩ፦ ኤርምያስ የይሁዳ ሰዎች ለከለዳውያን እጃቸውን መስጠት እንዳለባቸው የሚናገረውን የአምላክ መልእክት ሲያውጅ ከፍተኛ ተቃውሞ አጋጠመው።

1 ሁኔታውን ለማስተዋል ሞክር።ኤርምያስ 38:1-5ን አንብብ።

ኤርምያስ ለይሁዳ ሰዎች መልእክቱን ሲናገር ምን ተሰምቶት የነበረ ይመስልሃል?

ኤርምያስ የይሖዋን የፍርድ መልእክት ሲያውጅ ድምፁ ምን ዓይነት ስሜት የሚንጸባረቅበት ይመስልሃል?

․․․․․

ጥልቅ ምርምር አድርግ።

ኤርምያስ መልእክቱን እንዲህ በድፍረት ሊናገር የቻለው ምን ዓይነት እምነት ስለነበረው ነው?

․․․․․

2 ሁኔታውን ለማስተዋል ሞክር።ኤርምያስ 38:6-13ን አንብብ።

እስቲ ጉድጓዱ ምን ያህል ስፋትና ጥልቀት እንዳለው እንዲሁም ውስጡ ምን ዓይነት ሽታ ሊኖረው እንደሚችል አስበህ ጻፍ።

․․․․․

ኤርምያስ ‘ጭቃው’ ውስጥ እየሰመጠ እያለ ምን ተሰምቶት ሊሆን ይችላል? (ቁጥር 6⁠ን በድጋሚ አንብብ።)

․․․․․

ጥልቅ ምርምር አድርግ።

ምርምር ማድረግ የምትችልባቸው መሣሪያዎችን በመጠቀም በጥንት ጊዜ ስለነበሩት ጉድጓዶች ከዚህ በፊት የማታውቃቸውን ነገሮች ለማወቅ ሞክር

․․․․․

አቤሜሌክ ኤርምያስን ለማዳን እንዲነሳሳ ያደረገው ምን ዓይነት እምነት የነበረው መሆኑ ነው? (ከቁጥር 7-9⁠ን በድጋሚ አንብብ።)

․․․․․

ሴዴቅያስ በመጀመሪያ የመኳንንቱን በኋላም አቤሜሌክ የተናገረውን ሐሳብ ሳያንገራግር የተቀበለው ለምንድን ነው? (ቁጥር 5⁠ን እና 10⁠ን በድጋሚ አንብብ።) ይህ ሁኔታ ስለ ሴዴቅያስ ባሕርይና ጽኑ እምነት የሌለው ስለመሆኑ ምን ይጠቁማል?

․․․․․

በታሪኩ ውስጥ ጽኑ እምነት እንዳላቸው ያሳዩት እነማን ናቸው? ጽኑ እምነት ያልነበራቸውስ እነማን ናቸው? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው?

․․․․․

3 ከዚህ ታሪክ ያገኘኸውን ትምህርት ተግባራዊ አድርግ። ከዚህ በታች ስለተዘረዘሩት ነገሮች ምን ትምህርት እንዳገኘህ ጻፍ፦

ስለ ድፍረት።

․․․․․

ስለ ጽኑ እምነት።

․․․․․

ይሖዋ፣ ያለ አንዳች ፍርሃት ለሚታዘዙት ሰዎች ስለሚያደርገው ጥበቃ።

․․․․․

የሚያስጨንቅ ሁኔታ ሲያጋጥምህ ጽኑ እምነት ያለህ መሆኑ ትክክለኛ የሆነውን ነገር እንድታደርግ ሊረዳህ የሚችለው እንዴት ነው?

․․․․․

4 ከዚህ ታሪክ ውስጥ ይበልጥ ትምህርት ያገኘህበት ሐሳብ የትኛው ነው? ለምን እንዲህ አልክ?

․․․․․

በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ሌሎች ጽሑፎች ለማግኘት የይሖዋ ምሥክሮችን ጠይቅ ወይም www.watchtower.org ተመልከት።