በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ለእውነተኛው አምልኮ ጥብቅና ቁም!

ለእውነተኛው አምልኮ ጥብቅና ቁም!

ለታዳጊ ወጣቶች

ለእውነተኛው አምልኮ ጥብቅና ቁም!

መመሪያ፦ ይህን መልመጃ ጸጥታ በሰፈነበት ቦታ ሆነህ ሥራ። ጥቅሶቹን ስታነብ በቦታው እንዳለህ አድርገህ አስብ። ሁኔታውን በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል እንዲሁም በታሪኩ ውስጥ የተጠቀሱት ሰዎች ሲነጋገሩ ድምፃቸውን ለመስማትና ስሜታቸውን ለመረዳት ሞክር። ታሪኩ ሕያው እንዲሆንልህ አድርግ።

ዋነኞቹ ባለ ታሪኮች፦ ኤልያስ፣ አክዓብ እና 450 የበኣል ነቢያት

ታሪኩ በአጭሩ፦ ይሖዋ ከበኣል እንደሚበልጥ ኤልያስ አረጋገጠ።

1 ሁኔታውን ለማስተዋል ሞክር።—1 ነገሥት 18:17-40ን አንብብ።

ኤልያስና የበኣል ነቢያት የነበራቸውን አቋቋምና እያንዳንዳቸው የሠሯቸው መሠዊያዎች የተቀመጡበትን ቦታ በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል ሞክር፤ ከዚያም ወደ አእምሮህ የመጣልህን ምስል በአንድ ወረቀት ላይ ሳል።

ከቁጥር 26 እስከ 29 በተገለጸው ትርምስ ላይ ምን ድምፅ “ይሰማሃል?”

_______

ኤልያስ የበኣልን ነቢያት ሲናገራቸው ምን ዓይነት የድምፅ ቃና የነበረው ይመስልሃል?

_______

2 ጥልቅ ምርምር አድርግ።

ኤልያስ ከአክዓብ ጋር ለመገናኘት ብሎም በመቶዎች የሚቆጠሩ የበኣል ነቢያትን የሚያሳፍር ነገር ለማድረግ ድፍረት ያስፈለገው ለምንድን ነው? (ፍንጭ፦ 1 ነገሥት 18:4, 13, 14⁠ን አንብብ።)

_______

ምርምር ማድረግ የምትችልባቸውን መሣሪያዎች በመጠቀም ስለ በኣል አምልኮ ለማወቅ ሞክር። ለምሳሌ አምልኳቸውን ሲያከናውኑ ምን የማድረግ ልማድ ነበራቸው? የበኣል አምልኮ በእስራኤላውያን ላይ ምን ተጽዕኖ አሳድሯል?

_______

ኤልያስ በይሖዋ መሠዊያ ዙሪያ ጉድጓድ ቆፍሮ በውኃ እንዲሞላ ያደረገው ለምን ይመስልሃል?

_______

3 ከዚህ ታሪክ ያገኘኸውን ትምህርት ተግባራዊ አድርግ። ከዚህ በታች ስለሰፈረው ሐሳብ ምን ትምህርት እንዳገኘህ ጻፍ፦

ለእውነተኛው አምልኮ ጥብቅና ለመቆም ስለሚያስፈልገው ድፍረት።

_______

እንዲህ ዓይነት ድፍረት የሚያሳዩ ሰዎች ስለሚያገኙት ጥቅም።

_______

ልትሠራበት የሚገባ ተጨማሪ ነገር።

ለእውነተኛው አምልኮ ጥብቅና በመቆም ረገድ በየትኞቹ ሁኔታዎች ድፍረት ማሳየት ያስፈልግሃል?

_______

4 ከዚህ ታሪክ ውስጥ ይበልጥ ትምህርት ያገኘህበት ሐሳብ የትኛው ነው? ለምንእንዲህ አልክ?

_______

በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ሌሎች ጽሑፎች ለማግኘት የይሖዋ ምሥክሮችን ጠይቅ ወይም www.watchtower.org ተመልከት።

[በገጽ 31 ላይ የሚገኝ ሣጥን]

የአውራጃ ስብሰባን በተመለከተ የቀረበ መረጃ

ከዚህ ዓመት ጀምሮ የአውራጃ ስብስባዎች የሚደረጉባቸው ቀኖችና ቦታዎች በመጠበቂያ ግንብ ላይ አይወጡም። መረጃዎቹን jw.org በተባለው ድረ ገጽ ላይ ማግኘት ይቻላል።