በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በዛሬው ጊዜ የሚያጋጥሙንን ችግሮች ለመቋቋም እርዳታ ማግኘት የምንችለው ከየት ነው?

በዛሬው ጊዜ የሚያጋጥሙንን ችግሮች ለመቋቋም እርዳታ ማግኘት የምንችለው ከየት ነው?

ልዩ የሕዝብ ንግግር

በዛሬው ጊዜ የሚያጋጥሙንን ችግሮች ለመቋቋም እርዳታ ማግኘት የምንችለው ከየት ነው?

በዛሬው ጊዜ ስለማንኛውም ጉዳይ ምክር ማግኘት ይቻላል። የራስን ችግር በራስ መፍታት ስለሚቻልበት መንገድ የሚናገሩ መጻሕፍትና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች የብዙዎችን ቀልብ እየሳቡ ነው። ይሁንና አሁንም ቢሆን መሠረታዊ የሆኑ ችግሮችን መቅረፍ አልተቻለም። እርስዎም ‘አስተማማኝ መመሪያ ማግኘት የምችልበት ምንጭ ይኖር ይሆን?’ የሚል ጥያቄ ያነሱ ይሆናል። መልሱ ‘አዎን!’ የሚል ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ ከተጻፈ በሺህ የሚቆጠሩ ዓመታት ያለፉ ቢሆንም ለበርካታ ጥያቄዎች መልስ የሚሆኑ ዘመን የማይሽራቸው መመሪያዎችን ይዟል፤ ከእነዚህ መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦

▪ አለመግባባቶችን መፍታትም ሆነ ከሌሎች ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲኖረኝ ማድረግ የምችለው እንዴት ነው?

▪ ደስታ ማግኘት የምችለው እንዴት ነው?

▪ የኢኮኖሚ ችግሮችን መቋቋም የምችለው እንዴት ነው?

▪ የሚያስጨንቁ ሁኔታዎችን መቀነስ የምችለው እንዴት ነው?

“የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎች በዛሬው ጊዜ የሚያጋጥሙንን ችግሮች እንድንቋቋም ሊረዱን ይችላሉ?” በሚለው የሕዝብ ንግግር ላይ የእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ይብራራል። በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተው ይህ ንግግር በዓለም ዙሪያ ከ230 በሚበልጡ አገሮች ይቀርባል። በብዙ ቦታዎች ንግግሩ የሚቀርበው እሁድ፣ ሚያዝያ 23, 2003 (እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ግንቦት 1, 2011) በየአካባቢው በሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች የመንግሥት አዳራሽ ውስጥ ነው።

የስብሰባውን ጊዜና ቦታ በተመለከተ በአካባቢዎ የሚገኙት የይሖዋ ምሥክሮች መረጃ ሊሰጥዎት ፈቃደኛ ናቸው። በስብሰባው ላይ እንዲገኙ ሞቅ ያለ ግብዣ እናቀርብልዎታለን።