በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“የሰው ልጆች ምድራችንን ያጠፏት ይሆን?”

“የሰው ልጆች ምድራችንን ያጠፏት ይሆን?”

“የሰው ልጆች ምድራችንን ያጠፏት ይሆን?”

● ምድር ከሕዋ ላይ ስትታይ ሰማያዊና ነጭ ቀለም ያለው ፈርጥ ትመስላለች። ይሁንና ቀረብ ብለው ሲመለከቷት መኖሪያችን አደጋ እንደተጋረጠባት ታስታውቃለች። ለምን? መልሱ ቀላል ነው፦ የሰው ልጆች የሚኖሩባትን ምድር አልተንከባከቧትም። ሰዎች መኖሪያ ፕላኔታቸውን በመበከል፣ ደኖቿን በማራቆትና ሀብቷን በመመዝበር ቃል በቃል ምድርን ማበላሸታቸው ሳያንስ ሥነ ምግባራዊና መንፈሳዊ አቋማቸውን በዓመፅ፣ በደም መፋሰስና በፆታ ብልግና አበላሽተውታል።

ወደ ሁለት ሺህ ከሚጠጉ ዓመታት በፊት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሰፈሩ አስደናቂ ትንቢቶች ይህ ዓይነቱ አስከፊ ሁኔታ እንደሚከሰት አስቀድመው ተናግረዋል። (2 ጢሞቴዎስ 3:1-5፤ ራእይ 11:18) ከዚህም በተጨማሪ ከአምላክ በቀር ማንኛውም ሰው በምድር ላይ የደረሰውን ጉዳት ሙሉ በሙሉ ማስተካከል እንደማይችል መጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ተናግሯል። “የሰው ልጆች ምድራችንን ያጠፏት ይሆን?” የሚለው የሕዝብ ንግግር እነዚህን አስፈላጊ ርዕሰ ጉዳዮች በጥልቀት ያብራራል። ይህ ንግግር በግንቦት ወር ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በሚጀምረውና ከዚያም በኋላ በሌሎች የዓለም ክፍሎች በሚካሄደው “የአምላክ መንግሥት ይምጣ!” በተሰኘው የይሖዋ ምሥክሮች የአውራጃ ስብሰባ ላይ ይቀርባል።

እርስዎም በአቅራቢያዎ በሚደረገው የአውራጃ ስብሰባ ላይ እንዲገኙ በአክብሮት ጋብዘንዎታል። ዝርዝር መረጃ ለማግኘት እባክዎን በአካባቢዎ ያሉትን የይሖዋ ምሥክሮች ያነጋግሩ፤ አሊያም ለዚህ መጽሔት አዘጋጆች ይጻፉ። በተጨማሪም ስብሰባው በተለያዩ አገሮች መቼና የት እንደሚካሄድ የሚገልጽ ፕሮግራም www.pr418.com በሚለው ድረ ገጽ ላይ ይገኛል።