በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ለክፋት ድርጊቶች ተጠያቂ የሆነ አካል አለ?

ለክፋት ድርጊቶች ተጠያቂ የሆነ አካል አለ?

ለክፋት ድርጊቶች ተጠያቂ የሆነ አካል አለ?

“ከዲያብሎስ ጋር ስምምነት አድርጌአለሁ።” ይህ ሐሳብ በሩዋንዳ የተባበሩት መንግሥታት ሠራዊት አዛዥ የነበረ ሰው፣ በ1994 በዚያ አገር ይካሄድ የነበረውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ ማቆም አለመቻላቸውን አስታውሶ የተናገረው ነው። በዚያን ጊዜ የነበረውን ለማመን የሚያዳግት አረመኔያዊ ድርጊት የታዘበ ሌላ ሰው ደግሞ “ሰይጣን የለም ለማለት የሚዳዳው ሰው ካለ ሩዋንዳ በሚገኝ የጅምላ መቃብር እንገናኝ” ብሏል። እንዲህ ያለው የጭካኔ ድርጊት በእርግጥ የዲያብሎስ ሥራ ነው?

በርካታ ሰዎች ዛሬ ለምናየው ግፍና ጭካኔ ተጠያቂው በዓይን የማይታይ አንድ ክፉ መንፈሳዊ ፍጡር መሆኑን መቀበል ይከብዳቸዋል። ብዙዎች እንዲህ ያሉ ድርጊቶች በተፈጥሮ ከወረስነው ክፋት የሚመነጩ እንደሆኑና የክፋት ዋነኛ መንስኤ የራሳችን መጥፎ ዝንባሌ እንደሆነ ያስባሉ። ሌሎች ደግሞ ሀብታምና ተሰሚነት ያላቸው ሰዎች ዓለምን ለመግዛት ሲሉ እነሱ ወደሚፈልጉት አቅጣጫ ሰዎችን ለበርካታ ዓመታት በመጠምዘዝ፣ በግልጽ በማይታይ ሁኔታ በዓለም ዙሪያ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ ይሰማቸዋል። ለሚታየው የፍትሕ መጓደልና መከራ መንግሥታትንና ገዥዎችን ተጠያቂ የሚያደርጉ ሰዎችም አሉ።

አንተስ ምን ይመስልሃል? ሰዎች ክፋትን፣ ጭካኔን፣ አረመኔያዊ ድርጊትንና መከራን ለማስወገድ ጥረት ቢያደርጉም በዛሬው ጊዜ በዓለም ዙሪያ እነዚህ ነገሮች ተስፋፍተው የሚገኙት ለምንድን ነው? የሰው ዘር በተደጋጋሚ ለሚሰጠው ማስጠንቀቂያ ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት ለጥፋት ወደሚዳርገው ጎዳና በጭፍን እያመራ ያለው ለምንድን ነው? ከዚህ ሁሉ በስተጀርባ ተጠያቂ የሆነ አካል አለ? በእርግጥ ዓለምን እየገዛ ያለው ማን ነው? የዚህ ጥያቄ መልስ ያስገርምህ ይሆናል።