በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በሐሰት ተወንጅሏል!

በሐሰት ተወንጅሏል!

ለታዳጊ ወጣቶች

በሐሰት ተወንጅሏል!

ዮሴፍ​ክፍል 2

መመሪያ፦ ይህን መልመጃ ጸጥታ በሰፈነበት ቦታ ሆነህ ሥራ። ጥቅሶቹን ስታነብ በቦታው እንዳለህ አድርገህ አስብ። ሁኔታውን በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል እንዲሁም በታሪኩ ውስጥ የተጠቀሱት ሰዎች ሲነጋገሩ ድምፃቸውን ለመስማትና ስሜታቸውን ለመረዳት ሞክር። ታሪኩ ሕያው እንዲሆንልህ አድርግ።

ዋነኞቹ ባለ ታሪኮች፦ ዮሴፍ፣ ጲጥፋራና የጲጥፋራ ሚስት

ታሪኩ በአጭሩ፦ ዮሴፍ ፍትሕ በጎደለው መንገድ ታሰረ፤ ይሖዋ ግን ከእሱ ጋር ነበር።

1 ሁኔታውን ለማስተዋል ሞክር።​ዘፍጥረት 39:7, 10-23ን አንብብ።

የጲጥፋራ ሚስት ዮሴፍን በሐሰት ስትወነጅለው ስሜቷን የገለጸችው እንዴት ይመስልሃል?

․․․․․

ወኅኒ ቤቱ ምን ሊመስል እንደሚችል በዓይነ ሕሊናህ ለመሳልና ያሰብከውን ለመግለጽ ሞክር።

․․․․․

ዮሴፍ መጀመሪያ ወደ እስር ቤት በገባበት ጊዜ ምን ዓይነት ሁኔታዎችን በጽናት ማሳለፍ አስፈልጎት ነበር? (ፍንጭ፦ መዝሙር 105:17, 18⁠ን ተመልከት።)

․․․․․

2 ጥልቅ ምርምር አድርግ።

ዮሴፍ እምነቱ ደካማ ቢሆን ኖሮ እስር ቤት ውስጥ እያለ ምን ዓይነት የተሳሳተ መደምደሚያ ላይ ሊደርስ ይችል ነበር? (ፍንጭ፦ ኢዮብ 30:20, 21⁠ን ተመልከት።)

․․․․․

ዮሴፍ በደረሰበት መከራ የተነሳ በይሖዋ ላይ እንዳላማረረ እንዴት ማወቅ እንችላለን? (ፍንጭ፦ ዘፍጥረት 40:8፤ 41:15, 16⁠ን ተመልከት።)

․․․․․

ዮሴፍ ያለ ጥፋቱ በታሰረበት ወቅት ለመጽናት የረዱት ባሕርያት የትኞቹ ይመስሉሃል? (ፍንጭ፦ የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብብና አሰላስልባቸው፦ ሚክያስ 7:7፤ ሉቃስ 14:11፤ ያዕቆብ 1:4)

․․․․․

ዮሴፍ እስር ቤት ውስጥ እያለ ምን ዓይነት ሥልጠና አግኝቶ ነበር፤ ይህ ሥልጠናስ ከጊዜ በኋላ የጠቀመው እንዴት ሊሆን ይችላል? (ፍንጭ፦ ዘፍጥረት 39:21-23፤ 41:38-43⁠ን ተመልከት።)

․․․․․

3 ከዚህ ታሪክ ያገኘኸውን ትምህርት ተግባራዊ አድርግ። ከዚህ በታች ስለተዘረዘሩት ነገሮች ምን ትምህርት እንዳገኘህ ጻፍ፦

ችግሮችን በጽናት የሚቋቋሙ ሰዎች ስለሚያገኟቸው ጥቅሞች።

․․․․․

አስቸጋሪ ሁኔታዎችን በመቋቋምህ ልታገኝ ስለምትችለው ሥልጠና።

․․․․․

በፈተና ወቅት ይሖዋ ስለሚያደርግልህ ድጋፍ።

․․․․․

ልትሠራበት የሚገባ ተጨማሪ ነገር።

ችግር ውስጥ እንደወደቅህ ወይም እንደተገለልክ አንዲሰማህ የሚያደርግ ሁኔታ አጋጥሞህ ያውቃል? ከሆነ ፈተና እየደረሰብህ በነበረበት ጊዜም እንኳ ይሖዋ የረዳህ በየትኞቹ መንገዶች ሊሆን ይችላል? (ፍንጭ፦ 1 ቆሮንቶስ 10:13⁠ን አንብብና አሰላስል።)

․․․․․

4 ከዚህ ታሪክ ውስጥ ይበልጥ ትምህርት ያገኘህበት ሐሳብ የትኛው ነው? ለምን እንዲህ አልክ?

․․․․․

በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ሌሎች ጽሑፎች ለማግኘት የይሖዋ ምሥክሮችን ጠይቅ ወይም www.watchtower.org ተመልከት።