በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ይህን ያውቁ ኖሯል?

ይህን ያውቁ ኖሯል?

ይህን ያውቁ ኖሯል?

በኢየሩሳሌም በነበረው የይሖዋ ቤተ መቅደስ ውስጥ ለሚከናወነው አገልግሎት የሚያስፈልገው ገንዘብ ይገኝ የነበረው እንዴት ነው?

በቤተ መቅደሱ ውስጥ ለሚካሄዱት አብዛኞቹ አገልግሎቶች የገንዘብ ድጋፍ የሚገኘው ከሕዝቡ ከሚሰበሰብ ግብር ሲሆን በዋነኝነት ደግሞ ከሁሉም ሰው ከሚጠበቅ አሥራት ነበር። ሆኖም ሌሎች የግብር ዓይነቶችም ነበሩ። ለምሳሌ ያህል፣ የመገናኛው ድንኳን በተሠራበት ወቅት “ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መሥዋዕት” ወይም መዋጮ እንዲሆን ግማሽ ሰቅል ብር ከእያንዳንዱ የተመዘገበ እስራኤላዊ እንዲሰበስብ ይሖዋ ለሙሴ ነግሮት ነበር።​—ዘፀአት 30:12-16

ከዚያ ጊዜ በኋላ እያንዳንዱ አይሁዳዊ መጠኑ የተወሰነ ዓመታዊ የቤተ መቅደስ ግብር መክፈሉ ልማድ የሆነ ይመስላል። ኢየሱስ፣ ጴጥሮስን ከዓሣው አፍ በተገኘው ሳንቲም ይህን ግብር እንዲከፍል አዝዞት ነበር።​—ማቴዎስ 17:24-27

የቤተ መቅደሱን ግብር ለመክፈል ያገለግሉ የነበሩት ዓይነት ሁለት የብር ሳንቲሞች ከተወሰኑ ዓመታት በፊት በኢየሩሳሌም ተገኝተዋል። አንደኛው ሳንቲም በ22 ዓ.ም. ጢሮስ ውስጥ የተሠራ ሲሆን የተገኘው በመጀመሪያው መቶ ዘመን በተሠራ የውኃ መውረጃ ቱቦ ውስጥ ነው። ይህ ሰቅል በአንድ በኩል የጢሮስ ዋነኛ አምላክ የሆነው የመልካርት ወይም የበኣል ምስል በሌላ በኩል ደግሞ በአንድ መርከብ የፊተኛ ክፍል ላይ የተቀመጠ ንስር ተቀርጾበታል። ሁለተኛው ሳንቲም አይሁዳውያን በሮም ላይ ባመፁበት የመጀመሪያ ዓመት ላይ ማለትም ከ66-67 ዓ.ም. ይጠቀሙበት የነበረ ሲሆን በቤተ መቅደሱ ፍርስራሽ ውስጥ የተገኘ ነው። ሳንቲሙ ላይ የጽዋ እና ሦስት የሮማን ፍሬዎች ምስል ተቀርጾበታል፤ “ግማሽ ሰቅል” እና “ቅዱስ ኢየሩሳሌም” የሚል ጽሑፍም ሰፍሮበታል። ይህንን ግኝት አስመልክተው ፕሮፌሰር ጋብርዬል ባርኬ እንዲህ ብለዋል፦ “ሳንቲሙ . . . እሳት አቃጥሎት እንደነበር የሚጠቁሙ ምልክቶች ይታዩበታል፤ ይህም በ70 ዓ.ም. ሁለተኛውን ቤተ መቅደስ ያጠፋው እሳት የተወው አሻራ ሊሆን ይችላል።”

የባቢሎን ንጉሥ የነበረው ናቡከደነፆር ያከናወናቸው የግንባታ ፕሮጀክቶች ምን ያህል አስደናቂ ነበሩ?

የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በሆነው የዳንኤል መጽሐፍ ላይ ናቡከደነፆር “በብርቱ ኀይሌ፣ ለገናናው ክብሬ ንጉሣዊ መኖሪያ ትሆን ዘንድ ያሠራኋት ታላቂቷ ባቢሎን ይህች አይደለችምን?” በማለት እንደተናገረ እናነብባለን። (ዳንኤል 4:30) ይህች ጥንታዊት ከተማ በእርግጥ ያን ያህል ታላቅ ነበረች?

የታሪክ ምሁራን ናቡከደነፆር ቤተ መቅደሶችን፣ ቤተ መንግሥቶችን፣ የከተማ ግንቦችን እንዲሁም ገደላማ በሆነ ቦታ ላይ እንዳለ ሆኖ የተሠራ አስደናቂ የአትክልት ስፍራ እንደገነባ ይናገራሉ። በከተማይቱ እምብርት ይገኝ የነበረው ዋነኛው ቤተ መቅደስ ግዙፍ በሆነ ፒራሚድ አናት ላይ የተሠራ ሲሆን ከ70 ሜትር በላይ ከፍታ እንደነበረው ይገመታል። ይሁንና “ከፍተኛ አድናቆት ያተረፉት [የናቡከደነፆር] ሥራዎች የሰልፍ ጎዳና እና የኢሽታር በር ናቸው” በማለት ባቢሎን​የአስደናቂ ነገሮች ከተማ (እንግሊዝኛ) የተሰኘው መጽሐፍ ይናገራል። የባቢሎን የሰልፍ ጎዳና በኢሽታር በር በኩል የሚያልፍ ሲሆን በቀኝና በግራ በኩል ያሉት ግድግዳዎች እየተራመዱ ባሉ አንበሶች ምስል ያጌጡ ናቸው። ይኸው መጽሐፍ ስለ ታላቁ የባቢሎን መግቢያ ማለትም ስለ ኢሽታር በር ሲናገር እንዲህ ይላል፦ “በሚያብረቀርቁ ደማቅ ሰማያዊ ጡቦች የተሸፈነ ሲሆን ግድግዳው በመቶዎች በሚቆጠሩ ኮርማዎችና ድራገኖች ምስል አሸብርቋል፤ በወቅቱ ዋና ከተማዋን ለመጎብኘት የመጣ ሰው መግቢያው ላይ የሚመለከተውን ነገር እንደማይረሳው የታወቀ ነው።”

በ20ኛው መቶ ዘመን መጀመሪያ ላይ የአርኪኦሎጂ ባለሙያዎች የባቢሎንን የሰልፍ ጎዳናም ሆነ የኢሽታርን በር በሺዎች የሚቆጠሩ ፍርስራሾች በቁፋሮ ያገኙ ሲሆን በበርሊን፣ ጀርመን በሚገኘው ጴርጋሞን ቤተ መዘክር ውስጥ አብዛኞቹን ፍርስራሾች እንደገና ገንብተዋቸዋል።

[በገጽ 12 ላይ የሚገኙ ሥዕሎች]

ትክክለኛ መጠኑ

[የሥዕሉ ምንጭ]

Top: Clara Emit, Courtesy of Israel Antiquities Authority; bottom: Zev Radovan

[በገጽ 12 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

በድጋሚ የተገነባው የኢሽታር በር