በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ለታዳጊ ወጣቶች

ከክፉ መናፍስት ራስህን ጠብቅ!

ከክፉ መናፍስት ራስህን ጠብቅ!

መመሪያ፦ ይህን መልመጃ ጸጥታ በሰፈነበት ቦታ ሆነህ ሥራ። ጥቅሶቹን ስታነብ በቦታው እንዳለህ አድርገህ አስብ። ሁኔታውን በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል እንዲሁም በታሪኩ ውስጥ የተጠቀሱት ሰዎች ሲነጋገሩ ድምፃቸውን ለመስማትና ስሜታቸውን ለመረዳት ሞክር። ታሪኩ ሕያው እንዲሆንልህ አድርግ።

1 ሁኔታውን ለማስተዋል ሞክር።​—ዘፍጥረት 6:1-6ን እና የሐዋርያት ሥራ 19:11-20ን አንብብ።

ኔፊሊሞቹ ምን ዓይነት መልክና ቁመና ያላቸው ይመስልሃል?

․․․․․

በሐዋርያት ሥራ 19:13-16 ላይ የተገለጹት ሰዎች ክፉ መንፈስ ካጋጠማቸው በኋላ ምን የተሰማቸው ይመስልሃል?

․․․․․

2 ጥልቅ ምርምር አድርግ።

ምርምር ማድረግ የምትችልባቸውን መሣሪያዎች በመጠቀም ስለ ኔፊሊሞች ይበልጥ ለማወቅ ሞክር። እንዲህ ያለ የዓመፀኝነት መንፈስ የተጠናወታቸው ለምን ይመስልሃል?

․․․․․

ክፉ መናፍስት “ትክክለኛ መኖሪያቸውን የተዉት” እንዴት ነው? (ይሁዳ 6⁠ን አንብብ።) የሰው ልጆችን ሚስት ለማድረግ መፈለጋቸው ከተፈጥሮ ውጭ የሆነ አልፎ ተርፎም አስነዋሪ ድርጊት ነው የምትለው ለምንድን ነው?

․․․․․

ያነበብካቸው ሁለት ዘገባዎች ክፉ መናፍስት የፆታ ብልግናንና ዓመፅን እንደሚወዱ የሚያሳዩት እንዴት ነው?

․․․․․

3 ከዚህ ታሪክ ያገኘኸውን ትምህርት ተግባራዊ አድርግ። ከዚህ በታች ስለሰፈረው ሐሳብ ምን ትምህርት እንዳገኘህ ጻፍ፦

ክፉ መናፍስት ጨካኞችና ራስ ወዳዶች ስለ መሆናቸው

․․․․․

ልትሠራበት የሚገባ ተጨማሪ ነገር፦

ክፉ መናፍስት ሥጋ መልበስ ባይችሉም በየትኞቹ መንገዶች በአንተ ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር ሊሞክሩ ይችላሉ?

․․․․․

በአሁኑ ጊዜ የክፉ መናፍስትን ዝንባሌና ፍላጎት የሚያንጸባርቁ ምን ዓይነት መዝናኛዎች አሉ?

․․․․․

ክፉ መናፍስት የሚያሳድሩትን ተጽዕኖ ለመቋቋም መቁረጥህን በየትኞቹ መንገዶች ማሳየት ትችላለህ? (የሐዋርያት ሥራ 19:18, 19ን በድጋሚ አንብብ።)

․․․․․

4 ከእነዚህ ታሪኮች ውስጥ ልብህን ይበልጥ የነካው ምንድን ነው? ለምንስ?

․․․․․

በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ሌሎች ጽሑፎች ለማግኘት የይሖዋ ምሥክሮችን ጠይቅ ወይም www.watchtower.org ተመልከት።