በእርስዎ አመለካከት ኢየሱስ . . .
በእርስዎ አመለካከት ኢየሱስ . . .
አራስ ሕፃን ነው? ሞት አፋፍ ላይ ያለ ሰው ነው? ወይስ ክብር የተጎናጸፈ ንጉሥ?
መጽሐፍ ቅዱስ፣ ኢየሱስ ኃያል ንጉሥ እንደሆነ ይናገራል። ታዲያ ይህ ለእርስዎ ምን ትርጉም አለው?
ብዙ ሰዎች ኢየሱስ እንደሞተላቸው ያምናሉ። ሆኖም አንድ ሰው ከ2,000 ዓመታት ገደማ በፊት መሞቱ በዛሬው ጊዜ ለሚኖሩ ሰዎች መዳን የሚያስገኘው እንዴት ነው?
ለእነዚህ ጥያቄዎች መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን መልስ እንዲያዳምጡ በአክብሮት ተጋብዘዋል። ይህ ሐሳብ የሚብራራው የይሖዋ ምሥክሮች የኢየሱስን ሞት መታሰቢያ በሚያከብሩበት ዕለት ነው። በዚህ ዓመት በዓሉ የሚከበረው ሐሙስ፣ መጋቢት 27, 2004 (April 5, 2012) ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ነው።
ትክክለኛውን ሰዓትና ቦታ ለማወቅ እባክዎ በአካባቢዎ የሚኖሩ የይሖዋ ምሥክሮችን ያነጋግሩ።
የኢየሱስ ሞት መታሰቢያ ከተከበረ በኋላ ባለው እሁድ “መጨረሻው ሳታስቡት ይመጣባችሁ ይሆን?” የሚል ጭብጥ ያለው በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ ትኩረት የሚስብ ንግግር በይሖዋ ምሥክሮች የመሰብሰቢያ ቦታዎች ይቀርባል። ይህ ንግግር፣ የይሖዋ ምሥክሮች በዓለም ዙሪያ እውነትን የሚወዱና ስለ ኢየሱስ ይበልጥ ለማወቅ የሚፈልጉ ሰዎችን ለማግኘት በሚያደርጉት ጥረት ውስጥ የጎላ ቦታ ይሰጠዋል። እርስዎም በዚህ ንግግር ላይ እንዲገኙ በአክብሮት ተጋብዘዋል።