በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ጸሎትን የሚሰማ አካል አለ?

ጸሎትን የሚሰማ አካል አለ?

ጸሎትን የሚሰማ አካል አለ?

“አምላክ ስለ መኖሩ ጥርጣሬ ነበረኝ። ያም ቢሆን አንዳንድ ጊዜ እጸልያለሁ። ስጸልይ የሚሰማኝ ስለመኖሩ እርግጠኛ ባልሆንም ጸሎቴን የሚሰማ አካል በኖረ ብዬ እመኝ ነበር። ሕይወቴ ትርጉም የሌለው ከመሆኑም ሌላ ደስተኛ አልነበርኩም። በአምላክ የሚያምኑት ደካማ ሰዎች ብቻ እንደሆኑ ስለማስብ በአምላክ ለማመን እፈራ ነበር።”​—ፓትሪሻ፣ * አየርላንድ

አንተስ እንደ ፓትሪሻ ይሰማሃል? አምላክ ስለ መኖሩ ጥርጣሬ ቢኖርህም እንኳ ትጸልያለህ? ከሆነ እንዲህ የምታደርገው አንተ ብቻ አይደለህም። እስቲ ቀጥሎ የቀረቡትን ሐሳቦች ተመልከት፦

▪ በ2,200 ብሪታንያውያን ላይ የተደረገ ጥናት እንዳረጋገጠው ዓለምን የፈጠረና ጸሎትን የሚሰማ መንፈሳዊ አካል ያለው አምላክ እንዳለ የሚያምኑት 22 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ናቸው። ሆኖም ጥናት ከተካሄደባቸው መካከል 55 በመቶ የሚሆኑት ቢያንስ፣ አልፎ አልፎ እንደሚጸልዩ ተናግረዋል።

▪ በአራት አህጉራት በሚኖሩ 10,000 ሰዎች ላይ የተደረገ ጥናት እንዳሳየው በአምላክ መኖር እንደማያምኑ ከተናገሩት ሰዎች መካከል ወደ 30 በመቶ የሚጠጉት ይጸልያሉ።

አምላክ መኖሩን የሚጠራጠሩት ለምንድን ነው?

አለን የሚባል አንድ እንግሊዛዊ እንዲህ ይላል፦ “ሃይማኖት ሰዎችን ለመቆጣጠርና ገንዘብ ለማግኘት የተፈጠረ ነገር እንደሆነ ስለማስብ በአምላክ መኖር እንደማላምን እናገር ነበር። በተጨማሪም ‘አምላክ ቢኖር ኖሮ ይህ ሁሉ የፍትሕ መዛባት አይኖርም’ ብዬ አስብ ነበር። ያም ቢሆን አንዳንድ ጊዜ ብቻዬን ስሆን ወደ ‘አንድ ነገር’ እጸልይ ነበር። እንዲሁም ‘ሕልውና ያገኘሁት እንዴት ነው?’ ብዬ ራሴን እጠይቅ ነበር።”

እንዲህ የሚሰማው ማንኛውም ሰው፣ የሚያቀርበው ጸሎት መልስ ስለማግኘቱ እንዲጠራጠር የሚያደርገው የራሱ ምክንያት አለው። ለአንዳንድ ጥያቄዎቹ መልስ አለማግኘቱ ደግሞ አብዛኛውን ጊዜ ጥርጣሬው እንዲባባስ ያደርገዋል። ለምሳሌ እንደሚከተሉት ያሉ ጥያቄዎች ይኖሩት ይሆናል፦

▪ ፈጣሪ አለ?

▪ ሃይማኖት አብዛኛውን ጊዜ ለመጥፎ ነገሮች ምክንያት የሚሆነው ለምንድን ነው?

▪ አምላክ መከራና ሥቃይ እንዲኖር የፈቀደው ለምንድን ነው?

አንተስ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ብታገኝ ጸሎትን የሚሰማ አካል ስለ መኖሩ ይበልጥ እርግጠኛ ሆነህ መጸለይ የምትችል ይመስልሃል?

[የግርጌ ማስታወሻ]

^ አን.2 በእነዚህ ተከታታይ ርዕሶች ውስጥ የተጠቀሱት አንዳንዶቹ ስሞች ተቀይረዋል።