በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል ተማር

ኢየሱስ ንጉሥ ሆኖ መግዛት የጀመረው መቼ ነው?

ኢየሱስ ንጉሥ ሆኖ መግዛት የጀመረው መቼ ነው?

ይህ ርዕስ በአእምሮህ ሊመላለሱ የሚችሉ ጥያቄዎችን በማንሳት መልሶቹን መጽሐፍ ቅዱስህ ውስጥ የት ቦታ ላይ ማግኘት እንደምትችል ይጠቁምሃል። የይሖዋ ምሥክሮች ለጥያቄዎቹ በተሰጡት መልሶች ላይ ከአንተ ጋር ለመወያየት ፈቃደኞች ናቸው።

1. ኢየሱስ ንጉሥ ሆኖ እንደሚገዛበት አስቀድሞ የተነገረለት መንግሥት የትኛው ነው?

አምላክ፣ ከንጉሥ ዳዊት የዘር ሐረግ የሚመጣ ንጉሥ በእሱ ዙፋን ላይ ተቀምጦ ለዘላለም እንደሚገዛ አስቀድሞ ተናግሯል። አስቀድሞ የተነገረለት ይህ የዳዊት ዝርያ ኢየሱስ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ የአምላክ መንግሥት ንጉሥ ሆኖ በሰማይ እየገዛ ነው።​—መዝሙር 89:4ን እና ሉቃስ 1:32, 33ን አንብብ።

ይሖዋ፣ ሕዝቡን ማለትም እስራኤላውያንን እንዲያስተዳድር ዳዊትን ንጉሥ አድርጎ የመረጠው ገና ትንሽ ልጅ ሳለ ነበር። ዳዊት ሲሞት፣ አምላክ ንጉሥ እንዲሆን የመረጠው ሰለሞን “በእግዚአብሔር ዙፋን” ላይ ተቀመጠ። (1 ዜና መዋዕል 28:4, 5፤ 29:23) ሰለሞን ከሞተ በኋላም በኢየሩሳሌም በርካታ ነገሥታት ሥልጣን ላይ ወጥተዋል፤ አብዛኞቹ ግን ለይሖዋ ታማኞች አልነበሩም። በመሆኑም ይሖዋ፣ ባቢሎናውያን ኢየሩሳሌምን እንዲያጠፉና በዚያ የሚገዛውን ንጉሥ ከሥልጣኑ እንዲያወርዱት ፈቀደ። ይህ ሁኔታ የተፈጸመው በ607 ዓ.ዓ. ነው። ከዚያን ጊዜ በኋላ ከዳዊት የዘር ሐረግ የመጣ ንጉሥ በኢየሩሳሌም ተቀምጦ አልገዛም።​—ሕዝቅኤል 21:27ን አንብብ።

2. በምድር ላይ የአምላክን መንግሥት የሚወክል አገዛዝ ያልነበረው ለምን ያህል ጊዜ ነው?

ኢየሩሳሌም ከጠፋች ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ይሖዋ፣ ከሰማይ ሆኖ የሚገዛ ንጉሥ እንደሚያስነሳ ለነቢዩ ዳንኤል ነገረው። ታዲያ ይህ ንጉሥ መግዛት የሚጀምረው መቼ ነው?​—ዳንኤል 7:13, 14ን አንብብ።

አምላክ አንድ ትልቅ ዛፍ እንዲቆረጥ ትእዛዝ እንደሰጠ የሚገልጸው ራእይ ምን ትርጉም እንዳለው ዳንኤል ተናግሮ ነበር፤ የዛፉ መቆረጥ አምላክ በኢየሩሳሌም ሆኖ የሚገዛው መንግሥት እንዲቆረጥና እንዲጠፋ ማዘዙን የሚያመለክት ነበር። ዛፉ ቢቆረጥም “ሰባት ዘመናት” (የ1954 ትርጉም) ካለፉበት በኋላ እንደገና እንዲበቅል ሲባል ጉቶው መሬት ውስጥ እንዲቆይ ተደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ፣ ሦስት ተኩል “ዘመናት” ከ1,260 ቀናት ጋር እኩል እንደሆኑ ስለሚናገር “ሰባት ዘመናት” 2,520 ቀናትን ያመለክታሉ። (ራእይ 12:6, 14) መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሰፈሩት ትንቢቶች መሠረት ደግሞ ቀናት አብዛኛውን ጊዜ ዓመታትን ይወክላሉ። (ዘኍልቍ 14:34) በመሆኑም ለ2,520 ዓመታት በምድር ላይ የአምላክን መንግሥት የሚወክል ንጉሥ አይኖርም።​—ዳንኤል 4:10-17ን አንብብ።

3. ኢየሱስ የነገሠው መቼ ነው?

አምላክ፣ ኢየሱስን በሰማይ ያነገሠው በ1914 ይኸውም ኢየሩሳሌም ከጠፋች ልክ ከ2,520 ዓመታት በኋላ ነው። ኢየሱስ ንጉሥ ሆኖ እንደተሾመ መጀመሪያ የወሰደው እርምጃ ሰይጣንንና አጋንንቱን ከሰማይ ማባረር ነበር። (ራእይ 12:7-10) ከምድር ሆኖ ይህ ሁኔታ ሲፈጸም ያየ ሰው ባይኖርም ይህ ክንውን በጉልህ የሚታይ ለውጥ ይኸውም በሰው ልጆች ላይ መከራ አስከትሏል። (ራእይ 12:12) ከ1914 ወዲህ የታዩት ክስተቶች ኢየሱስ መግዛት የጀመረው በዚሁ ዓመት እንደሆነ ያረጋግጣሉ።​—ማቴዎስ 24:14ን እና ሉቃስ 21:10, 11, 31ን አንብብ።

4. ኢየሱስ ንጉሥ ሆኖ መሾሙ ለአንተ ምን ትርጉም አለው?

ኢየሱስ ንጉሥ ሆኖ ስለ መሾሙ የሚናገሩት ትንቢቶች መፈጸማቸው በአምላክ ቃል ላይ እምነት መጣል እንደምትችል ያሳያል። በቅርቡ ኢየሱስ ንጉሣዊ ሥልጣኑን በመጠቀም በሰው ዘር ላይ የሚደርሰውን መከራ በሙሉ ያስወግዳል።​—መዝሙር 72:8, 12, 13ን እና ዳንኤል 2:44ን አንብብ።

ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ተመልከት።

[በገጽ 16, 17 ላይ የሚገኝ ሰንጠረዥ]

(መልክ ባለው መንገድ የተቀናበረውን ለማየት ጽሑፉን ተመልከት)

ጥቅምት

607 ዓ.ዓ. ← 2,520 ዓመታት → 1914 ዓ.ም.

1000 ዓ.ዓ. | 1 ዓ.ዓ. 1 ዓ.ም. | 1000 ዓ.ም. | 1000 ዓ.ም. | 2000 ዓ.ም.

← 606 ዓመት ከ3 ወር →← 1,913 ዓመት ከ9 ወር →

በኢየሩሳሌም የነበረው መንግሥት ጠፋ

የሚከተለውን አስላ606 ዓመት ከ3 ወር + 1,913 ዓመት ከ9 ወር = 2,520

አምላክ፣ ኢየሱስን በአሕዛብ ላይ እንዲገዛ ንጉሥ አድርጎ ሾመው