መጠበቂያ ግንብ ኅዳር 2012 | አምላክን ምን መጠየቅ ትፈልጋለህ?
መጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ጊዜ ለሚነሱ 3 ጥያቄዎች የሚሰጠውን መልስ ማወቅ ትፈልጋለህ? ጥያቄዎቹ የሚከተሉት ናቸው፦ ሕይወት ዓላማ አለው? ስንሞት ምን እንሆናለን? አምላክ መከራ እንዲኖር የፈቀደው ለምንድን ነው?
የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ
አምላክን መጠየቅ ተገቢ ነው?
በሕይወታችን ውስጥ ለሚነሱብን አንገብጋቢ ጥያቄዎች የሚያረካ መልስ ማግኘት የምንችለው ከየት ነው? አምላክን መጠየቅ እንችላለን?
የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ
ጥያቄ 1፦ ሕይወቴ ዓላማ አለው?
ብዙ ሰዎች፣ በሕይወታችን ውስጥ ቅድሚያ ልንሰጣቸው የሚገቡ ነገሮች ገንዘብና ዝና እንደሆኑ ይሰማቸዋል፤ እውነቱን ለመናገር ግን ከእነዚህ የሚበልጡ ብዙ ነገሮች አሉ።
የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ
ጥያቄ 2፦ ስሞት ምን እሆናለሁ?
ብዙዎች ‘ከሞትን በኋላ ምን እንሆናለን?’ የሚለው ነገር ያስፈራቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ ይህን በተመለከተ የሚያስተምረውን ለማወቅ ይህን ርዕስ አንብብ።
የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ
ጥያቄ 3፦ አምላክ መከራ እንዲደርስብኝ የሚፈቅደው ለምንድን ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ፣ በሰዎች ላይ ለሚደርሰው መከራ አምላክ ተጠያቂ እንዳልሆነ በግልጽ ይናገራል። ታዲያ በንጹሐን ሰዎች ላይ መከራ የሚደርሰው ለምንድን ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎችን ሕይወት ይለውጣል
ጥሩ ገቢ የሚያስገኝ ሥራ የነበራት ሴት፣ ቁማርተኛ የነበረ ሰው እንዲሁም የሕይወት ትርጉም ጠፍቶት የነበረ ሰው እውነተኛ ደስታ ማግኘት የቻሉት እንዴት ነው?
ይህን ያውቁ ኖሯል?
በጥንት ዘመን የሚኖሩ ሰዎች የተጠቀሙት ምን ዓይነት ብዕርና ቀለም ነበር? ሐዋርያው ጳውሎስ ይሠራ የነበረው ምን ዓይነት ድንኳኖችን ነው?
ከአምላክ ቃል ተማር
አምላክ መላውን ምድር የሚያስተዳድር አንድ መንግሥት ያቋቁማል?
የሰው ዘር የሚያጋጥሙት አብዛኞቹ ችግሮች ዓለም አቀፋዊ ይዘት አላቸው። ዓለም አቀፋዊ የሆነ መስተዳድር መኖሩ ችግሩን ያስወግደው ይሆን?
ወደ አምላክ ቅረብ
‘ይሖዋ ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው?’
አምላክ፣ እሱን ማምለክ ከሚፈልጉ ሰዎች ምን ይጠብቃል? ፍጽምና የሚጎድላቸው ሰዎች አምላክን ማስደሰት ይችላሉ?
አንባቢያን የሚያነሱት ጥያቄ
እምነት ለማዳበር የሚጥር ሰው ራሱን እያታለለ ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ የሚያበረታታን በጭፍን እንድናምን ሳይሆን የማሰብ ችሎታችንን ተጠቅመን ማስረጃዎቹን እንድንመረምር ነው።
መጽሐፍ ቅዱስን መማሪያዬ
ዝናብ እንዲዘንብ የሚያደርገው ማን ነው? ዝናብ የሚያስፈልገንስ ለምንድን ነው? ስለ አምላክና እሱ ስለፈጠራቸው ነገሮች ለልጆችህ ለማስተማር ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ ተጠቀም።
በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን የነበረው ሕይወት—እረኛው
የጥንት እረኞች የትኞቹን እንስሳት ይጠብቁ ነበር? ሥራቸውስ ምን ነገሮችን ይጨምር ነበር?
የአውሮፓ ፍርድ ቤት በወታደራዊ አገልግሎት ለመካፈል ሕሊናቸው የማይፈቅድላቸውን ሰዎች መብት አስከበረ
በሌሎች የአውሮፓ አገሮች ለሚነሱ ተመሳሳይ ጉዳዮች ትክክለኛ ፍርድ ለመስጠት የሚያስችል መሠረት የሚሆነውን ይህን ታሪካዊ ብይን አስመልክቶ የቀረበውን ዘገባ እንድታነብ እንጋብዝሃለን።