በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

የሰው ልጆች ወደፊት ምን ይጠብቃቸዋል?

ኢየሱስ መሞቱ፣ ሰዎች እርስ በርሳቸው የሚተሳሰቡበት ማኅበረሰብ እንዲኖር መንገድ የከፈተው እንዴት ነው?

የሰው ልጆች በሳይንስ መስክ እድገት ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉ ጥያቄ የለውም። ይሁንና እርስ በርስ ከልብ የሚተሳሰቡ ሰዎች ያሉበት ማኅበረሰብ እንዲኖር ማድረግ ይችሉ ይሆን? በፍጹም። በዛሬው ጊዜ በዓለም ላይ ራስ ወዳድነትና ስግብግብነት ነግሷል። ሆኖም የአምላክ ዓላማ የሰው ዘር የተሻለ ሕይወት እንዲኖረው ነው።2 ጴጥሮስ 3:13ን አንብብ።

ወደፊት፣ እርስ በርስ የሚዋደዱ ሰዎች ያሉበት ዓለም አቀፋዊ ማኅበረሰብ እንደሚኖር የአምላክ ቃል ይናገራል። ሰዎች ያለ ስጋት የሚኖሩ ሲሆን ጉዳት የሚያደርስባቸውም አይኖርም።ሚክያስ 4:3, 4ን አንብብ።

ራስ ወዳድነት የሚወገደው እንዴት ነው?

የሰው ልጅ መጀመሪያ ሲፈጠር የራስ ወዳድነት ዝንባሌ ፈጽሞ አልነበረውም። ይሁንና የመጀመሪያው ሰው፣ አምላክን ባለመታዘዙ ፍጽምናውን አጣ። እኛም የራስ ወዳድነት ዝንባሌን ከእሱ ወረስን። ያም ቢሆን አምላክ በኢየሱስ አማካኝነት የሰው ልጆች ወደ ፍጽምና ደረጃ እንዲደርሱ ያደርጋል።ሮም 7:21, 24, 25ን አንብብ።

ኢየሱስ ከአምላክ ፈቃድ ጋር በሚስማማ መንገድ መሥዋዕት ሆኖ በመሞት የመጀመሪያው ሰው ዓመፅ ያስከተለውን ውጤት አስወግዷል። (ሮም 5:19) በመሆኑም ኢየሱስ፣ ሰዎች መጥፎ ነገር እንዲያደርጉ ከሚገፋፋ የራስ ወዳድነት ዝንባሌ ነፃ የመሆን ግሩም ተስፋ እንዲኖራቸው አድርጓል።መዝሙር 37:9-11ን አንብብ።