መዝሙር 11
ፍጥረት ይሖዋን ያወድሳል
(መዝሙር 19)
-
1. ይሖዋ ሆይ፣ ድንቅ ነው ፍጥረትህ፤
ያውጃሉ ሰማያት ክብርህን።
ቃል ባይኖርም፣ ድምፃቸው ባይወጣም፣
መል’ክታቸው አስተጋባ ባለም።
ቃል ባይኖርም፣ ድምፃቸው ባይወጣም፣
መል’ክታቸው አስተጋባ ባለም።
-
2. ጥበብ አለው አንተን ’ሚፈራ ሰው፤
ንግግሩ፣ ድርጊቱ ንጹሕ ነው።
ት’ዛዛትህ ከወርቅ ይበልጣሉ፤
ለትሑታን ጥበብ ይሰጣሉ።
ት’ዛዛትህ ከወርቅ ይበልጣሉ፤
ለትሑታን ጥበብ ይሰጣሉ።
-
3. ትርጉም ያለው ሕይወት የምንመራው
መመሪያህን ስለምንጠብቅ ነው።
ለሚያከብሩ ታላቁን ስምህን
ታሳያቸዋለህ ሞገስህን።
ለሚያከብሩ ታላቁን ስምህን
ታሳያቸዋለህ ሞገስህን።
(በተጨማሪም መዝ. 12:6፤ 89:7፤ 144:3ን እና ሮም 1:20ን ተመልከት።)