በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 116

ደግነት ያለው ኃይል

ደግነት ያለው ኃይል

(ኤፌሶን 4:32)

  1. 1. አምላክ ሆይ፣ ከልብ እናወድስህ፤

    ስለ ባሕርያትህ።

    ታላቅ ቢሆንም ኃይልህ፣ ጥበብህ

    ወደር የለው ደግነትህ።

  2. 2. ሸክም ከብዷቸው የደከሙትን

    ልጅህ ጋብዟቸዋል።

    ቀንበሩ ልዝብ፣ ሸክሙ ቀላል ነው፤

    ማጽናኛ ከሱ ይገኛል።

  3. 3. አምላክንና ’የሱስን መምሰል፣

    ፍላጎታችን ነው።

    አዛኞችና ደጎች እንሁን፤

    ደግነት ትልቅ ኃይል አለው።

(በተጨማሪም ሚክ. 6:8⁠ን፣ ማቴ. 11:28-30⁠ን፣ ቆላ. 3:12⁠ን እና 1 ጴጥ. 2:3⁠ን ተመልከት።)