በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 13

ምሳሌያችን የሆነው ክርስቶስ

ምሳሌያችን የሆነው ክርስቶስ

(1 ጴጥሮስ 2:21)

  1. 1. የይሖዋን ፍቅር

    ጥሩነቱን አየን፤

    የበኩር ልጁን ለኛ ሲልክልን።

    ኢየሱስ ሰው ሆኖ

    በምድር ላይ ኖረ፤

    የይሖዋንም ስም አስከበረ።

  2. 2. ሕይወት ለሚያስገኘው፣

    ጥበብ ለሚሰጠው

    ለይሖዋ ቃል አድናቆት ነበረው።

    አባቱን ማስደሰት

    እርካታ ሰጥቶታል፤

    በዚህም ለኛ ምሳሌ ትቷል።

  3. 3. ይሖዋን ማስደሰት

    ነው ፍላጎታችን፤

    መሪያችን ኢየሱስ ነው ምሳሌያችን።

    በልጁ ምሳሌ

    እስከሄድን ድረስ

    እናገኛለን ያምላክን ሞገስ።

(በተጨማሪም ዮሐ. 8:29⁠ን፣ ኤፌ. 5:2⁠ን እና ፊልጵ. 2:5-7⁠ን ተመልከት።)