በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 131

“አምላክ ያጣመረውን”

“አምላክ ያጣመረውን”

(ማቴዎስ 19:5, 6)

  1. 1. በደስታ፣ በክብር

    ተገመደ በሦስት።

    ባምላክና በሰው ፊት፣

    ቃል ኪዳን ገባላት።

    (አዝማች 1)

    በአምላክ ፊት ማለላት፤

    ከልቡ ሊወዳት።

    ‘አምላክ ያጣመረውን፣

    ማንም አይለያየው።’

  2. 2. መርምረዋል ቃሉን፤

    ለማድረግ ፈቃዱን።

    እርዳታውን ይሻሉ፤

    ታማኞች ለመሆን።

    (አዝማች 2)

    በአምላክ ፊት ቃል ገባች፤

    ከልቧ ልትወደው።

    ‘አምላክ ያጣመረውን፣

    ማንም አይለያየው።’

(በተጨማሪም ዘፍ. 2:24⁠ን፣ መክ. 4:12⁠ን እና ኤፌ. 5:22-33⁠ን ተመልከት።)