በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 146

‘ሁሉንም ነገር አዲስ ያደርጋል’

‘ሁሉንም ነገር አዲስ ያደርጋል’

(ራእይ 21:1-5)

  1. 1. የአምላክ መንግሥት መግዛቱን ጀምሯል።

    የይሖዋ ልጅ ሥልጣኑን ይዟል።

    ከሰማይ ላይ ሰይጣንን አባሯል፤

    በምድርም ያምላክ ፈቃድ ይሆናል።

    (አዝማች)

    ተስፋው እንዴት ያስደስታል!

    አምላክ ከሰዎች ጋር ያድራል።

    ሐዘን፣ ሥቃይ አይኖርም ጨርሶ፤

    ይወገዳል ሞት፣ እንባና ለቅሶ።

    ‘ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ’ ብሏል፤

    እውነት ነው፤ ይፈጸማል።

  2. 2. አዲሷን ’የሩሳሌም ይዩ ሰዎች፤

    የበጉ ሙሽራ ተውባለች።

    የከበረ ዕንቁ ሰጣት ድምቀት፤

    ይሖዋ አምላክ ሆነላት መብራት።

    (አዝማች)

    ተስፋው እንዴት ያስደስታል!

    አምላክ ከሰዎች ጋር ያድራል።

    ሐዘን፣ ሥቃይ አይኖርም ጨርሶ፤

    ይወገዳል ሞት፣ እንባና ለቅሶ።

    ‘ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ’ ብሏል፤

    እውነት ነው፤ ይፈጸማል።

  3. 3. በሮቿ የማይዘጉ ቀን ከሌት፤

    ይቺ ከተማ የሰው ልጅ ሐሴት።

    ከሷ በሚፈነጥቀው ብርሃን፣

    ሕዝቦች ይጓዙ አይተው ጸዳሏን።

    (አዝማች)

    ተስፋው እንዴት ያስደስታል!

    አምላክ ከሰዎች ጋር ያድራል።

    ሐዘን፣ ሥቃይ አይኖርም ጨርሶ፤

    ይወገዳል ሞት፣ እንባና ለቅሶ።

    ‘ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ’ ብሏል፤

    እውነት ነው፤ ይፈጸማል።

(በተጨማሪም ማቴ. 16:3⁠ን፣ ራእይ 12:7-9⁠ን እና 21:23-25⁠ን ተመልከት።)