በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 158

‘አይዘገይ ከቶ!’

‘አይዘገይ ከቶ!’

(ዕንባቆም 2:3)

  1. 1. ተሠርታ ባንተ፣

    ድንቅ እጹብ ሆና፤

    ምድርን የሚገልጽ

    ምን ቃል ይገኝና!

    ቢያበላሻት ሰው

    የ’ጅህን ሥራ፣

    ታስውባታለህ

    ልክ እንደ ሙሽራ።

    (አዝማች)

    አባት ሆይ ናፈቀን፣

    መኖር እፎይ ብለን፤

    ት’ግሥቱን ’ባክህ ስጠን።

    የጓጓንለት ቀን

    እናያለን መጥቶ፤

    ምን ቢቆይ፣ ምን ቢረዝም፣

    ‘አይዘገይ ከቶ!’

  2. 2. ሞት የረታቸው

    ካፈር ሲወጡ፣

    መች ይሆን ደርሶ

    ’ምናየው ሲመጡ?

    ሁንልን ጉልበት

    ሌቱ ’ስኪነጋ፤

    እንድንታገሥ

    ይሖዋ ካንተ ጋ።

    (አዝማች)

    አባት ሆይ ናፈቀን፣

    መኖር እፎይ ብለን፤

    ት’ግሥቱን ’ባክህ ስጠን።

    የጓጓንለት ቀን

    እናያለን መጥቶ፤

    ምን ቢቆይ፣ ምን ቢረዝም፣

    ‘አይዘገይ ከቶ!’

  3. 3. ስተው ከመንገድ

    የተጨነቁ፣

    በመታገሥህ

    ስምህን አወቁ።

    ብርሃን ለዓለም፣

    አንተ ነህ ተስፋ፤

    ብንደክምልህ፣

    ክብር ነው ብንለፋ።

    (አዝማች)

    አባት ሆይ ናፈቀን፣

    መኖር እፎይ ብለን፤

    ት’ግሥቱን ’ባክህ ስጠን።

    የጓጓንለት ቀን

    እናያለን መጥቶ፤

    ምን ቢቆይ፣ ምን ቢረዝም፣

    ‘አይዘገይ ከቶ!’

    ስጠን ታጋሽ ልብ ’ባክህ!

(በተጨማሪም ቆላ. 1:11ን ተመልከት።)