መዝሙር 159
ለይሖዋ ክብር ስጡ
1. ማን አለ ’ንዳንተ ይሖዋ?
አቻ የለህ አምሳያ።
ማን አለ ’ንዳንተ ገናና?
የግርማ ሞገስ ማደሪያ።
የሚያስደምም ነው ዙፋንህ፤
በክብርህ የሞላኸው።
ታስበው ዘንድ ሰው ምንድን ነው?
እንዲህ ቦታ የሰጠኸው?
(አዝማች)
ይሖዋ ሆይ፣ አምላኬ፣ ንጉሤ፣
ልቀኝልህ ምስጋና።
ያስደስትህ የባሪያህ ዝማሬ፤
ላወድስህ በዜማ።
ክብር ያንተ ነውና!
2. ደግ አባት ነህ፣ እጅግ መልካም፤
እኔ የ’ጅህ ባለ’ዳ።
ላውራ ’ንጂ ልናገርልህ፤
አልከፍለው ያንተን ውለታ።
ሕይወቴን ሰጥቼሃለሁ፤
የለም የምሰስተው።
ባሪያህ ልሁን፣ ላገልግልህ፤
ክብሬ ነው መሆኔ ያንተው።
(አዝማች)
ይሖዋ ሆይ፣ አምላኬ፣ ንጉሤ፣
ልቀኝልህ ምስጋና።
ያስደስትህ የባሪያህ ዝማሬ፤
ላወድስህ በዜማ።
ክብር ያንተ ነውና!
3. አቤቱ የ’ጆችህ ሥራ!
ፀሐይ፣ ምድር፣ ጨረቃ።
ምሥክር ናቸው ለፍቅርህ፤
ያወድሱሃል ያለቃል።
ድንቅ ዕፁብ ውበት ለበሱ፤
ጥበብህ እንከን አልባ።
ሁሉን የፈጠርከው ጌታ፣
ክብርህ ይላቅ፣ ያስተጋባ።
(አዝማች)
ይሖዋ ሆይ፣ አምላኬ፣ ንጉሤ፣
ልቀኝልህ ምስጋና።
ያስደስትህ የባሪያህ ዝማሬ፤
ላወድስህ በዜማ።
ክብር ያንተ ነውና!
(በተጨማሪም መዝ. 96:1-10፤ 148:3, 7ን ተመልከት።)