በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 26

ለእኔ እንዳደረጋችሁት ይቆጠራል

ለእኔ እንዳደረጋችሁት ይቆጠራል

(ማቴዎስ 25:34-40)

  1. 1. የ’የሱስ የሆኑ ሌሎች በጎች አሉ፤

    ከቅቡዓኑ ጋር ’ሚያገለግሉ።

    ለቅቡዓኑ

    ’ሚያደርጉትን እርዳታ፣

    ’የሱስ ይቆጥረዋል እንደ ውለታ።

    (አዝማች)

    “እነሱን የረዳ እኔን ረድቶኛል፤

    ለነሱ ያ’ረገ ለኔ አድርጓል።

    ያስተናገዳቸው አስተናግዶኛል፤

    ያ’ረገላቸው ለኔም አድርጓል።

    እነሱን የረዳ እኔን ረድቶኛል።”

  2. 2. “ስቸገር አይታችሁ ደረሳችሁልኝ፤

    ሲርበኝ፣ ሲጠማኝ መገባችሁኝ።”

    “ይህን ያደረግነው

    መቼ ነው?” ይሉታል።

    ንጉሡም እንዲህ ብሎ ይመልሳል፦

    (አዝማች)

    “እነሱን የረዳ እኔን ረድቶኛል፤

    ለነሱ ያ’ረገ ለኔ አድርጓል።

    ያስተናገዳቸው አስተናግዶኛል፤

    ያ’ረገላቸው ለኔም አድርጓል።

    እነሱን የረዳ እኔን ረድቶኛል።”

  3. 3. “ከወንድሞቼ ጋር ሆናችሁ በመስበክ፣

    ታማኝ ሆናችኋል መልካም በማድረግ።”

    በቀኙ ላሉት

    እንዲህ ይላል ንጉሡ፦

    “ፍጹም ሕይወትና ምድርን ውረሱ።”

    (አዝማች)

    “እነሱን የረዳ እኔን ረድቶኛል፤

    ለነሱ ያ’ረገ ለኔ አድርጓል።

    ያስተናገዳቸው አስተናግዶኛል፤

    ያ’ረገላቸው ለኔም አድርጓል።

    እነሱን የረዳ እኔን ረድቶኛል።”

(በተጨማሪም ምሳሌ 19:17⁠ን፣ ማቴ. 10:40-42⁠ን እና 2 ጢሞ. 1:16, 17⁠ን ተመልከት።)