መዝሙር 52
ራስን ለአምላክ መወሰን
-
1. ይሖዋ ስለፈጠረ
ግዙፉን ጽንፋለም፣
ሰማይ፣ ምድር ንብረቱ ነው፤
የሱ ናቸው ሁሉም።
ሕይወት፣ እስትንፋስ ለሰጠን፣
ይድረስ ምስጋናችን።
ሊወደስ ሊመለክ ይገባል፤
ሁሉን በነፃ ሰጥቷል።
-
2. ጽድቅን ሊፈጽም ኢየሱስ
በውኃ ተጠምቋል።
በፈቃደኝነት ራሱን
ለአምላክ አቅርቧል።
ከዮርዳኖስ ውኃ ወጥቶ፣
በመንፈስ ሲቀባ፤
‘ፈቃድህን ማድረግ እሻለሁ’
ብሎ ላምላክ ቃል ገባ።
-
3. ይሖዋ ልናወድስህ
በፊትህ ቀርበናል።
ከልብ ራሳችንን ክደን
ላንተ ወስነናል።
በውድ ዋጋ ተገዝተናል፤
የልጅህ ደም ፈሷል።
ብንኖር፣ ብንሞት ያንተው ነን፤
አበቃ የራስ መሆን።