መዝሙር 59
ያህን አብረን እናወድስ
-
1. ያህን አብረን
እናወድስ!
ሰጥቶናል ሕይወትና እስትንፋስ።
ስሙን እንባርክ፣
ሌትና ቀን።
እንናገር ሁሉን ቻይ መሆኑን፤
እንዘምር፣ እናሳውቅ ስሙን።
-
2. ያህን አብረን
እናወድስ!
ጸሎት ሰምቶ ይሰጣልና መልስ።
ደካማውን
ይደግፋል፤
ለትሑታን መንፈሱን ይሰጣል።
’ናውጃለን ያለውን ታላቅ ኃይል።
-
3. ያህን አብረን
’ናወድሰው!
ያጽናናናል፣ የፍትሕ አምላክ ነው።
ልባችንን
ይጠግናል፤
በረከቱን ለሁሉም ያፈሳል።
ኑ በደስታ እንበልለት እልል።
(በተጨማሪም መዝ. 94:18, 19፤ 145:21፤ 147:1፤ 150:2ን እና ሥራ 17:25ን ተመልከት።)