መዝሙር 84
እገዛ የሚያስፈልጋቸውን መርዳት
-
1. አምላክ ያውቃል ’ሚበጀንን፣
ደስታ፣ ስኬት ’ሚሰጠንን።
ለማገልገል የሚያስችለን
ብዙ መንገድ ከፈተልን።
(አዝማች)
እገዛ ሲያስፈልግ
ሄደን እንርዳ።
ምርጣችንን እንስጥ፤
አለብን የፍቅር ዕዳ።
-
2. ሁሉም አገር አለ ሥራ፤
ይፈለጋል የኛ ’ርዳታ።
አሳቢነት በማሳየት
እንችላለን ማገዝ፣ መርዳት።
(አዝማች)
እገዛ ሲያስፈልግ
ሄደን እንርዳ።
ምርጣችንን እንስጥ፤
አለብን የፍቅር ዕዳ።
-
3. ባቅራቢያችን ባለ ቦታ
እንካፈል በግንባታ።
ለሰው ሁሉ ለመመሥከር
እንዲያስችለን ቋንቋ ’ንማር።
(አዝማች)
እገዛ ሲያስፈልግ
ሄደን እንርዳ።
ምርጣችንን እንስጥ፤
አለብን የፍቅር ዕዳ።