መዝሙር 147
ልዩ ንብረት
-
አምላክ አዲስ ፍጥረቱን፣
የተቀቡ ልጆቹን፣
ከሰው መሃል ዋጃቸው፤
ሞገሱን ሰጣቸው።
(አዝማች)
ለስምህ ’ሚሆን ሕዝብ፣
ልዩ ንብረትህ ናቸው።
’ሚወዱህ፣ ’ሚያከብሩህ፤
ዝናህን ’ሚያውጁ አንድ ሆነው።
-
ቅዱስ ብሔር ሆነዋል፤
የ’ውነትን ቃል ይዘዋል።
የሱን ብርሃን እንዲያዩ
አምላክ ጠርቷቸዋል።
(አዝማች)
ለስምህ ’ሚሆን ሕዝብ፣
ልዩ ንብረትህ ናቸው።
’ሚወዱህ፣ ’ሚያከብሩህ፤
ዝናህን ’ሚያውጁ አንድ ሆነው።
-
ምሥራቹን በመስበክ
ሌሎች በጎችን ጠሩ።
ታማኝ ናቸው ለበጉ፣
ት’ዛዙን ’ሚያከብሩ።
(አዝማች)
ለስምህ ’ሚሆን ሕዝብ፣
ልዩ ንብረትህ ናቸው።
’ሚወዱህ፣ ’ሚያከብሩህ፤
ዝናህን ’ሚያውጁ አንድ ሆነው።
(በተጨማሪም ኢሳ. 43:20ለ, 21ን፣ ሚል. 3:17ን እና ቆላ. 1:13ን ተመልከት።)