በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አልኖርክም ገና!

አልኖርክም ገና!

አውርድ፦

  1. 1. ቀናነት የታል ባለም?

    ወርሶት የክፋት አረም።

    ዳገት ሆኗል መልካም ማድረግ።

    (ቅድመ አዝማች)

    አትኑር መስለህ ቃሉ ’ንዳለህ፤ ክፉን አሸንፍ ታግለህ።

    ይሖዋን ስማ፤ ትካሳለህ።

    (አዝማች)

    ማን አለ ያፈረ?

    እሱን አምኖ በነፍሱ፣ ማን ወድቆ ቀረ?

    ጽና፣ በል ጽና፤

    ሕይወት ካልክስ የምሩ፣ መች ተነካና!

    ምን አይተህ ዛሬማ? አልኖርክም ገና!

  2. 2. ስምህን ሲያነሳሱ፣

    ነገ ላይቀር ሊረሱህ፤

    አትሞኝ ሲያሞግሱህ።

    (ቅድመ አዝማች)

    ነፋስ ማሳደድ ነው ትርፉ፤ ያለም ዝና ነው ከንቱ!

    ይሖዋን ስማ፤ ትካሳለህ።

    (አዝማች)

    ማን አለ ያፈረ?

    እሱን አምኖ በነፍሱ፣ ማን ወድቆ ቀረ?

    ጽና፣ በል ጽና፤

    ሕይወት ካልክስ የምሩ፣ መች ተነካና!

    ምን አይተህ ዛሬማ? አልኖርክም ገና!

    (አዝማች)

    ማን አለ ያፈረ?

    እሱን አምኖ በነፍሱ፣ ማን ወድቆ ቀረ?

    ጽና፣ በል ጽና፤

    ሕይወት ካልክስ የምሩ፣ መች ተነካና!

    ምን አይተህ ዛሬማ? አልኖርክም ገና!