በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ዝም አንልም

ዝም አንልም

አውርድ፦

  1. 1. ቀርቧል ዓለም መጥፊያው፤

    ምልክቱ ግልጽ ነው።

    ግን ሰዎች እንዴት ይድናሉ

    ሳይደርሳቸው ቃሉ?

  2. 2. መፍራት የለብንም፤

    እውነትን አንደብቅም።

    እንለምን እሱን፣ እንጸልይ፤

    ድፍረት ይስጠን፣ አቅም።

    (አዝማች)

    እሳት ነው አይዳፈን፣

    የቃሉ ወላፈን፤

    አዎ፣ ዝም አንልም።

    ክብራማው ብርሃን ይብራ፤

    ለሰው እናጋራው።

    አዎ፣ ዝም አንልም፤

    ዝም አንልም!

  3. 3. የቻልነውን እናድርግ፤

    መስበክ ያበቃል በቅርብ።

    ያኔ ለአምላክ እንቆማለን፣

    ሁላችን አንድ ሆነን።

    (አዝማች)

    እሳት ነው አይዳፈን፣

    የቃሉ ወላፈን፤

    አዎ፣ ዝም አንልም።

    ክብራማው ብርሃን ይብራ፤

    ለሰው እናጋራው።

    አዎ፣ ዝም አንልም፤

    ዝም አንልም!

    (መሸጋገሪያ)

    እንግዲያው እንናገር፤ አናቁም ላፍታ፤

    ደርሷል፣ ቀርቧል ቀኑ፤ አይሰጥ ፋታ።

    እንበርታ!

    (አዝማች)

    እሳት ነው አይዳፈን፣

    የቃሉ ወላፈን፤

    አዎ፣ ዝም አንልም።

    ክብራማው ብርሃን ይብራ፤

    ለሰው እናጋራው።

    አዎ፣ ዝም አንልም፤

    ዝም አንልም!

    ዝም አንልም!

    ዝም አንልም!