በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ይቅርብን ጓዙ

ይቅርብን ጓዙ

አውርድ፦

  1. 1. ምን ቢያምር፣ ሲታይ ቢያጓጓ፤

    ቁሳቁስ ቤት እንጂ ልብ አይሞላ።

    ባሪያ ያደርገናል አገልጋይ፤

    አለቃ መግዛት በራስ ላይ።

    (አዝማች)

    ይቅርብን ጓዙ፣

    ሲበዛ ትርፉ ጣጣ፤

    ማቅለል ይበጃል፣ ያዋጣል።

    ይቅርብን ጓዙ፣

    ለ’ለት እንደሁ አናጣ፤

    ማቅለል ይበጃል፣ ያዋጣል።

  2. 2. ካለን ልብስ፣ መደረቢያ፣

    ጎጆ ላንገት ማስገቢያ፣

    ረክቶ መኖር ይሻላል በ’ለት ጉርስ፤

    ለየቅል ናቸው ደስታና ቁስ።

    (አዝማች)

    ይቅርብን ጓዙ፣

    ሲበዛ ትርፉ ጣጣ፤

    ማቅለል ይበጃል፣ ያዋጣል።

    ይቅርብን ጓዙ፣

    ለ’ለት እንደሁ አናጣ፤

    ማቅለል ይበጃል፣ ያዋጣል።

    (መሸጋገሪያ)

    ቃል ገብቷል ሊደግፈን፤

    አያሳጣንም ከቶ!

    አንድም ያፈረ የለም፤

    ይሖዋን ተመክቶ።

    ማንም በሱ ታምኖ።

  3. 3. ሸክም ሲቀል፣ ሩጫችን ሲሰክን፣

    ሐሳብ አይበተን፣ ልብም አይባክን።

    አቤት ደስ ሲል ነፃነቱ፤

    መስጠት መቻል ላምላክ ምርጡን።

    (አዝማች)

    ይቅርብን ጓዙ፣

    ሲበዛ ትርፉ ጣጣ፤

    ማቅለል ይበጃል፣ ያዋጣል።

    ይቅርብን ጓዙ፣

    ለ’ለት እንደሁ አናጣ፤

    ማቅለል ይበጃል።

    (አዝማች)

    ይቅርብን ጓዙ፣

    ሲበዛ ትርፉ ጣጣ፤

    ማቅለል ይበጃል፣ ያዋጣል።

    ይቅርብን ጓዙ፣

    ለ’ለት እንደሁ አናጣ፤

    ማቅለል ይበጃል፣ ያዋጣል።