ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ—ቪዲዮዎች
የማስተማር እንዲሁም ለሰዎች የማንበብ ችሎታህን ለማሻሻል የሚያስፈልጉህን ክህሎቶች ለማዳበር እነዚህን ቪዲዮዎች ተጠቀም።
ጥናት 3
ጥያቄዎችን መጠቀም
ጥያቄዎችን ተጠቅመን አሳማኝ በሆነ መንገድ ማስረዳት፣ የአድማጮችን ትኩረት መሳብ እንዲሁም ዋና ዋና ነጥቦችን ማጉላት የምንችለው እንዴት ነው?
ጥናት 6
የጥቅሱን ዓላማ ግልጽ ማድረግ
አድማጮችህ ጥቅሱን የጠቀስክበት ዓላማ ግልጽ እንዲሆንላቸው ለመርዳት ጥቅሱን በምታነብበት ጊዜና ካነበብክ በኋላ ምን ማድረግ ይኖርብሃል?
ጥናት 9
በሚታዩ ነገሮች ተጠቅሞ ማስተማር
አድማጮችህ አስፈላጊ የሆኑ ነጥቦችን መረዳት እንዲችሉ ሥዕሎችን ወይም ሌሎች የሚታዩ ነገሮችን መጠቀም የምትችለው እንዴት ነው?
ጥናት 13
የትምህርቱን ጥቅም ግልጽ ማድረግ
አንድን ርዕስ የትምህርቱን ጥቅም ግልጽ በሚያደርግና አድማጮችን ለተግባር በሚያነሳሳ መንገድ ማቅረብ የምትችለው እንዴት ነው?
ጥናት 14
ዋና ዋና ነጥቦች ጎላ ብለው እንዲታዩ ማድረግ
ዋና ዋና ነጥቦች ጎላ ብለው እንዲታዩ ማድረግ አድማጮችህ ንግግርህን በትኩረት እንዲከታተሉ፣ እንዲረዱትና እንዲያስታውሱት እርዳቸው።
ጥናት 16
አዎንታዊና የሚያበረታታ
በችግሮች ላይ ሳይሆን በመፍትሔያቸው ላይ ያተኮረና አድማጮችን ለተግባር የሚያነሳሳ ንግግር ለማቅረብ የሚረዱን ሦስት ወሳኝ ነገሮች ምንድን ናቸው?
ጥናት 18
ግንዛቤ የሚያሰፋ
አድማጮች ርዕሰ ጉዳዩን እንዲያስቡበት ብሎም ጠቃሚ ትምህርት እንዳገኙ እንዲሰማቸው በሚያደርግ መንገድ ትምህርቱን ማቅረብ የምትችለው እንዴት ነው?
እነዚህንስ አይተሃቸዋል?
መጻሕፍትና ብሮሹሮች
ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
ይህ ብሮሹር የተዘጋጀው ለሰዎች የማንበብ እንዲሁም የንግግርና የማስተማር ችሎታህን ለማሻሻል እንዲረዳህ ታስቦ ነው።