በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

Left: Olena Yefremkina/stock.adobe.com; center: lunamarina/stock.adobe.com; right: Rido/stock.adobe.com

ነቅታችሁ ጠብቁ!

ማንን ማመን ትችላለህ?—⁠መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ማንን ማመን ትችላለህ?—⁠መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 ሰዎች እምነት የሚጥሉባቸው አካላት ብዙውን ጊዜ እንደታመኑት ሆነው ሳይገኙ ይቀራሉ። በመሆኑም ብዙዎች እምነት እያጡ መጥተዋል፤ ለምሳሌ፣

  •   የፖለቲካ መሪዎችን ማመን ይከብዳቸዋል፤ ምክንያቱም ከሕዝብ ጥቅም ይልቅ የራሳቸውን ፍላጎት ያስቀድማሉ።

  •   መገናኛ ብዙኃንን ማመን ይቸገራሉ፤ ምክንያቱም ሚዛኑን በጠበቀና ሐቀኛ በሆነ መንገድ እውነታውን የማያቀርቡበት ጊዜ አለ።

  •   በሳይንስ ሊቃውንት ላይ እምነት መጣል ይቸገራሉ፤ ምክንያቱም አንዳንዶች የማኅበረሰቡን ደህንነት ለመጠበቅ ጥረት አያደርጉም።

  •   የሃይማኖት መሪዎችን ማመን ከብዷቸዋል፤ ምክንያቱም የአምላክ ወኪሎች መሆን ሲገባቸው በፖለቲካ ሲጠላለፉ ይታያሉ።

 ሰዎች ሌሎችን ከማመናቸው በፊት ጥንቃቄ ማድረጋቸው ተገቢ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ሲል ያስጠነቅቃል፦

  •   “ማዳን ስለማይችሉ በመሪዎች . . . አትተማመኑ።”​—መዝሙር 146:3 የ1980 ትርጉም

እምነት የሚጣልበት መሪ

  መጽሐፍ ቅዱስ እምነት ልንጥልበት የምንችል አካል እንዳለ ይጠቁማል፤ እሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ኢየሱስ ከብዙ ዘመናት በፊት እንዲሁ ኖሮ ያለፈ ጥሩ ሰው ብቻ አይደለም። በአምላክ የተሾመ መሪ ሲሆን “ንጉሥ ሆኖ ይገዛል፤ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም።” (ሉቃስ 1:32, 33) ኢየሱስ በአሁኑ ወቅት በሰማይ ሆኖ እያስተዳደረ ያለው የአምላክ መንግሥት ንጉሥ ነው።​—ማቴዎስ 6:10