በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

Comstock Images/Stockbyte via Getty Images

ምግባረ ብልሹ ፖለቲከኞች—የአምላክ መንግሥት ምን እርምጃ ይወስዳል?

ምግባረ ብልሹ ፖለቲከኞች—የአምላክ መንግሥት ምን እርምጃ ይወስዳል?

 ሰዎች እምነት የሚጣልበት መሪ ማግኘት ይፈልጋሉ፤ ምግባረ ብልሹ በሆኑ ፖለቲከኞች ምክንያት በጣም ተማርረዋል። በ2023 የወጣ ዓለም አቀፋዊ ጥናት እንደሚያሳየው፣ ሰዎች ለማመን እንደሚከብዳቸው ከገለጿቸው ቡድኖች ውስጥ የመጀመሪያውን ቦታ የሚይዙት የፖለቲካ መሪዎች ናቸው። a

 መጽሐፍ ቅዱስ ሙሉ በሙሉ እምነት የሚጣልበት፣ ሐቀኛና ከሙስና የጸዳ መሪ ስላለው አንድ አገዛዝ ይናገራል። ይህ አገዛዝ የአምላክ መንግሥት ሲሆን መሪውም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።—ኢሳይያስ 9:7

 ኢየሱስ ለሰዎች ከልብ እንደሚያስብ በተደጋጋሚ አስመሥክሯል። (ማቴዎስ 9:35, 36) የአምላክ መንግሥት ንጉሥ እንደመሆኑ መጠን የእሱን አገዛዝ ለሚቀበሉ ሁሉ ፍትሕና ሰላም ያሰፍናል።—መዝሙር 72:12-14

a የ2023 የኤድልመን ትረስት ባሮሜትር ዓለም አቀፋዊ ሪፖርት።