በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

Yan Zabolotnyi/stock.adobe.com

ነቅታችሁ ጠብቁ!

ሥርዓት አልበኝነት በዓለም ዙሪያ ጨምሯል—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ሥርዓት አልበኝነት በዓለም ዙሪያ ጨምሯል—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 የወሮበሎች ጥቃት ሄይቲን እየተፈታተናት ነው። ደቡብ አፍሪካ፣ ሜክሲኮ እና ሌሎች የላቲን አሜሪካ አገሮች ውስጥ ከባድ ወንጀሎች አስከፊ ደረጃ ላይ ደርሰዋል። ከባድ ወንጀል ያን ያህል ባልከፋባቸው አገሮችም እንኳ በዝርፊያ ወንጀሎች የተነሳ ሰዎች የደህንነት ስሜት ርቋቸዋል።

 መጽሐፍ ቅዱስ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች እየተከሰተ ስላለው ሥርዓት አልበኝነት ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሥርዓት አልበኝነት የተናገረው ትንቢት

 መጽሐፍ ቅዱስ በሚናገረው ትንቢት መሠረት ሥርዓት አልበኝነት “የዚህ ሥርዓት መደምደሚያ ምልክት” ከሆኑ ነገሮች አንዱ ነው። (ማቴዎስ 24:3) የዚህ ምልክት መገለጫ ስለሆኑ ክስተቶች ሲገልጽ ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፦

  •   “ሕገ ወጥነት እየበዛ ስለሚሄድ የብዙዎች ፍቅር ይቀዘቅዛል።”​—ማቴዎስ 24:12 የግርጌ ማስታወሻ

 “በመጨረሻዎቹ ቀናት” ሰዎች “ራሳቸውን የማይገዙ፣ ጨካኞች፣ ጥሩ ነገር የማይወዱ” እንደሚሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ አስቀድሞ ተናግሯል። (2 ጢሞቴዎስ 3:1-5) በአሁኑ ወቅት ለምንመለከተው ሥርዓት አልበኝነት ምክንያት ከሆኑ ነገሮች መካከል እንዲህ ያሉ የራስ ወዳድነት ባሕርያት ይገኙበታል።

 ነገር ግን ሁኔታው ጨርሶ ተስፋ የለውም ማለት አይደለም። በቅርቡ ሥርዓት አልበኝነት እንደሚወገድ መጽሐፍ ቅዱስ ተስፋ ይሰጣል።

  •   “ለጥቂት ጊዜ ነው እንጂ ክፉዎች አይኖሩም፤ በቀድሞ ቦታቸው ትፈልጋቸዋለህ፤ እነሱ ግን በዚያ አይገኙም። የዋሆች ግን ምድርን ይወርሳሉ፤ በብዙ ሰላምም እጅግ ደስ ይላቸዋል።”​—መዝሙር 37:10, 11

 መጽሐፍ ቅዱስ ስለሚሰጠው የተስፋ መልእክት ይበልጥ ብታውቅ ደስ ይልሃል? ዛሬ በዓለም ላይ የምናያቸው ነገሮች የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ፍጻሜ ናቸው የምንልባቸውን ተጨማሪ ማስረጃዎች መመልከትስ ትፈልጋለህ? ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ርዕሶች እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

 የተሻለ ጊዜ ይመጣል ብለን ተስፋ ማድረግ እንችላለን?

 ‘የመጨረሻዎቹ ቀናት’ ወይም ‘የመጨረሻው ዘመን’ ምልክት ምንድን ነው?

 መጽሐፍ ቅዱስ በዛሬው ጊዜ ስለሚኖሩ ሰዎች ባሕርይ እና ምግባር ትንቢት ተናግሯል?