በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

Ismail Sen/Anadolu Agency via Getty Images

ነቅታችሁ ጠብቁ!

አውዳሚ ርዕደ መሬት ቱርክንና ሶርያን መታ—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

አውዳሚ ርዕደ መሬት ቱርክንና ሶርያን መታ—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 ሰኞ፣ የካቲት 6, 2023 አውዳሚ ርዕደ መሬት ቱርክንና ሶርያን መቷል።

  •   “ከባድ ርዕደ መሬት በቱርክና በሶርያ ሰሜን ምዕራባዊ ክፍል ከ3,700 ለሚበልጡ ሰዎች ሕልፈት ምክንያት ሆኗል፤ ቀዝቃዛው የክረምት ወቅት ደግሞ በአደጋው ምክንያት ለቆሰሉና ቤት አልባ ለሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ችግሩን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ አድርጎታል፤ ሰዎችን ለማትረፍ የሚደረገውን ርብርብም እጅግ ፈታኝ አድርጎታል።”—ሮይተርስ፣ የካቲት 6, 2023

 እንዲህ ያሉ ዜናዎች ልብ ይሰብራሉ። በዚህ ወቅት “የመጽናናት ሁሉ አምላክ” የሆነው ይሖዋ እንደሚደግፈን መተማመን እንችላለን። (2 ቆሮንቶስ 1:3) “ተስፋ ይኖረን ዘንድ” አምላክ ‘በቅዱሳን መጻሕፍት’ አማካኝነት “መጽናኛ” ይሰጠናል።—ሮም 15:4

 መጽሐፍ ቅዱስ የሚከተሉትን መረጃዎች ይዟል፦

  •   የምድር ነውጦችን አስመልክቶ የተነገሩ ትንቢቶች

  •   መጽናኛና ተስፋ ከየት እንደሚገኝ

  •   አምላክ የሰውን ልጅ አበሳ የሚያስወግደው እንዴት እንደሆነ

 መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እነዚህ ነገሮች ምን እንደሚል ማወቅ ትፈልጋለህ? የሚከተሉትን ርዕሶች አንብብ፦

a ይሖዋ የአምላክ የግል ስም ነው።—መዝሙር 83:18