በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ነቅታችሁ ጠብቁ!

6 ሚሊዮን ሰዎች በኮቪድ ሕይወታቸውን አጥተዋል—መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ ጉዳይ ተናግሮ ይሆን?

6 ሚሊዮን ሰዎች በኮቪድ ሕይወታቸውን አጥተዋል—መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ ጉዳይ ተናግሮ ይሆን?

 የዓለም የጤና ድርጅት እንደገለጸው እስከ ግንቦት 23, 2022 ባለው ጊዜ ውስጥ 6.27 ሚሊዮን ሰዎች በኮቪድ-19 ምክንያት ሕይወታቸውን አጥተዋል። ሆኖም ግንቦት 5, 2022 ባወጣው ሪፖርት ላይ የሞቱት ሰዎች ብዛት ከዚህም እጅግ ሊበልጥ እንደሚችል ጠቁሟል። በ2020 እና 2021 “በቀጥታ በኮቪድ-19 ምክንያት ወይም ተያያዥነት ባላቸው ሌሎች ምክንያቶች የሞቱት ሰዎች ብዛት . . . 14.9 ሚሊዮን እንደሚደርስ” ሪፖርቱ ገምቷል። መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ አሳዛኝ ክስተት የተናገረው ነገር ይኖር ይሆን?

መጽሐፍ ቅዱስ ቀሳፊ ወረርሽኞች እንደሚከሰቱ አስቀድሞ ተናግሯል

  •    ኢየሱስ አስቀድሞ እንደተናገረው ‘የመጨረሻዎቹ ቀናት’ ተብሎ የሚጠራው ጊዜ ሲደርስ ቸነፈር ይከሰታል፤ በሌላ አባባል “በበሽታ ብዙ ሕዝብ ያልቃል።”—ሉቃስ 21:11 ሕያው ቃል፤ 2 ጢሞቴዎስ 3:1

 ኢየሱስ የተናገረው ትንቢት በዛሬው ጊዜ እየተፈጸመ ነው። ተጨማሪ ማብራሪያ ማግኘት ከፈለግህ “‘የመጨረሻዎቹ ቀናት’ ወይም ‘የመጨረሻው ዘመን’ ምልክት ምንድን ነው?” የሚለውን ርዕስ አንብብ።

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያጽናና ሐሳብ ይዟል

  •    “የመጽናናት ሁሉ አምላክ . . . በሚደርስብን መከራ ሁሉ ያጽናናናል።”—2 ቆሮንቶስ 1:3, 4

 የቤተሰባቸውን አባልና ወዳጃቸውን በሞት የተነጠቁ ብዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ ተጽናንተዋል። ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት “ሐዘንን መቋቋም—አሁን ልትወስዳቸው የምትችላቸው እርምጃዎች” እና “ሐዘን ለደረሰባቸው የሚሆን የላቀ ማጽናኛ” የሚሉትን ርዕሶች አንብብ።

መጽሐፍ ቅዱስ ለዘለቄታው መፍትሔ የሚገኘው እንዴት እንደሆነ ይናገራል

  •    “መንግሥትህ ይምጣ። ፈቃድህ በሰማይ እየተፈጸመ እንዳለ ሁሉ በምድርም ላይ ይፈጸም።”—ማቴዎስ 6:10

 በቅርቡ “የአምላክ መንግሥት” ምድርን ማስተዳደር ሲጀምር “ማንኛውም ሰው ‘ታምሜአለሁ’ አይልም።” (ማርቆስ 1:14, 15፤ ኢሳይያስ 33:24) በሰማይ ስለተቋቋመው ስለዚህ መንግሥትና ወደፊት ለሰው ልጆች ስለሚያደርጋቸው ነገሮች ማወቅ ከፈለግህ የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው? የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት።

 መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሚገኘውን ለአንተም ሆነ ለቤተሰብህ የሚጠቅም ምክር ማወቅ ትፈልጋለህ? ስለ ወደፊቱ ጊዜ የሚሰጣቸውን አስደሳች ተስፋዎችስ ማወቅ ትፈልጋለህ? መጽሐፍ ቅዱስን እንድትማር እንጋብዝሃለን