በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ነቅታችሁ ጠብቁ!

በመላው ዓለም የተስፋፋው በጦር መሣሪያ የሚፈጸም ጥቃት—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

በመላው ዓለም የተስፋፋው በጦር መሣሪያ የሚፈጸም ጥቃት—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 በሐምሌ ወር 2022 በጦር መሣሪያ አስደንጋጭ የሆኑ ወንጀሎች በመላው ዓለም ተፈጽመዋል፦

  •   “የጃፓን ታዋቂ ፖለቲከኛ [የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ] መገደል አገሪቱን አናውጧታል፤ በመላው ዓለምም ከፍተኛ ድንጋጤ ፈጥሯል። ሁኔታውን ይበልጥ አሳሳቢ ያደረገው ደግሞ ወንጀል እምብዛም ባልተስፋፋባትና ጥብቅ የመሣሪያ ቁጥጥር በሚደረግባት አገር እንዲህ ያለ ጥቃት መፈጸሙ ነው።”—ሐምሌ 10, 2022 ዘ ጃፓን ታይምስ

  •   ኮፐንሃገን ውስጥ ባለ የገበያ ማዕከል መሣሪያ የታጠቀ አንድ ሰው ሦስት ሰዎችን ተኩሶ መግደሉ በዴንማርክ መደናገጥ ፈጥሯል።”—ሐምሌ 4, 2022 ሮይተርስ

  •   “ደቡብ አፍሪካ፦ ሶዌቶ ውስጥ በአንድ መዝናኛ ክበብ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ 15 ሰዎች ተገደሉ።”—ሐምሌ 10, 2022 ዘ ጋርዲያን

  •   “ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ሐምሌ 4 በተከበረው በዓል ሰሞን ከ220 የሚበልጡ ሰዎች በጦር መሣሪያ ተገድለዋል።”—ሐምሌ 5, 2022 ሲ ቢ ኤስ ኒውስ

 እንዲህ ያለው ወንጀል የሚያበቃበት ጊዜ ይመጣ ይሆን? መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ወንጀል የሚያበቃበት ጊዜ ይመጣል

 መጽሐፍ ቅዱስ የምንኖርበትን ዘመን ‘የመጨረሻዎቹ ቀናት’ በማለት ይጠራዋል፤ በዚህ ዘመን የሚኖሩ ሰዎች ጭካኔ የተሞላባቸውና አረመኔያዊ ድርጊቶችን እንደሚፈጽሙ ይናገራል። (2 ጢሞቴዎስ 3:1, 3) እንዲህ ያሉት የወንጀል ድርጊቶች የሰዎች ሕይወት በፍርሃት የተሞላ እንዲሆን አድርገዋል። (ሉቃስ 21:11) ደስ የሚለው ግን መጽሐፍ ቅዱስ ወንጀል የሚያበቃበትና ሰዎች “ሰላማዊ በሆነ የመኖሪያ ስፍራ፣ አስተማማኝ በሆነ መኖሪያና ጸጥታ በሰፈነበት የማረፊያ ቦታ” የሚኖሩበት ጊዜ እንደሚመጣ ይናገራል። (ኢሳይያስ 32:18) ይሁንና ወንጀል የሚጠፋው እንዴት ነው?

 አምላክ ክፉ ሰዎችንም ሆነ የጦር መሣሪያዎችን በሙሉ ጠራርጎ ያጠፋቸዋል።

  •   “ክፉዎች ከምድር ገጽ ይጠፋሉ፤ ከዳተኞችም ከእሷ ይወገዳሉ።”—ምሳሌ 2:22

  •   “[አምላክ] ጦርነትን ከመላው ምድር ላይ ያስወግዳል። ቀስትን ይሰባብራል፤ ጦርንም ያነክታል፤ የጦር ሠረገሎችን በእሳት ያቃጥላል።”—መዝሙር 46:9

 አምላክ ሰዎች ሰላማዊ ሆነው እንዲኖሩ በማስተማር ለችግሩ ከሥረ መሠረቱ መፍትሔ ያበጅለታል።

  •   “በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት ወይም ጥፋት አያደርሱም፤ ምክንያቱም ውኃ ባሕርን እንደሚሸፍን ምድርም በይሖዋ እውቀት ትሞላለች።”—ኢሳይያስ 11:9

  •   በዛሬው ጊዜም እንኳ አምላክ በዓለም ዙሪያ ያሉ ሰዎችን ከወንጀል ድርጊቶች እንዲርቁና የጦር መሣሪያ እንዳይዙ እያስተማራቸው ነው፤ ከአምላክ የተማሩ ሰዎች “ሰይፋቸውን ማረሻ፣ ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ።”—ሚክያስ 4:3

 ፍርሃት የማይኖርበት ዓለም እንደሚመጣ ስለሚናገረው የመጽሐፍ ቅዱስ ተስፋ ማወቅ ትፈልጋለህ? “ከፍርሃት ነጻ መሆን ይቻላል?” የሚለውን ርዕስ አንብብ።

 ወንጀል ጨርሶ ስለሚወገድበት ጊዜ ለማወቅ “በመጨረሻ በምድር ላይ ሰላም ይሰፍናል! የሚለውን ርዕስ አንብብ።