ብቸኝነትን መቋቋም የሚቻልበት መንገድ
ብቸኝነት እየተሰማህ ነው? ከሆነ “በጣሪያ ላይ እንዳለች ብቸኛ ወፍ ሆንኩ” እንዳለው መዝሙራዊ ተሰምቶህ ይሆናል። (መዝሙር 102:7) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው ጥበብ የሚንጸባረቅበት ምክር ብቸኝነትን ለመቋቋም ይረዳሃል።
መንፈሳዊነትህን አሳድግ
ብቻህን ብትሆንም እንኳ መንፈሳዊ ፍላጎትህን ለማርካት ጥረት የምታደርግ ከሆነ ደስተኛ መሆን ትችላለህ። (ማቴዎስ 5:3, 6) ከዚህ በታች የተዘረዘሩት በነፃ የሚገኙ መሣሪያዎች ይህን ለማድረግ ይረዱሃል።
ትክክለኛና ለመረዳት ቀላል የሆነ ኢንተርኔት ላይ የሚገኝ መጽሐፍ ቅዱስ
ስለ መሠረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች የሚገልጹ አጫጭር ቪዲዮዎች
“የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው”—ብዙ ሰዎች ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች መልስ ይዟል
“በእምነታቸው ምሰሏቸው”—በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ ታማኝ ሰዎችን ታሪክ የያዙ ተከታታይ ርዕሶች
“ንድፍ አውጪ አለው?”—የተፈጥሮን ውበትና ውስብስብነት የሚያወሱ ተከታታይ ርዕሶች
የሚያጽናኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን አንብብ
በዓለም ላይ መጥፎ ነገሮች የሚደርሱበትን ምክንያት እወቅ
መጥፎ ነገሮች የሚደርሱበትን ምክንያት እንዲሁም አምላክ እነዚህን ችግሮች የሚያስወግድበትን መንገድ ማወቅህ የትኛውንም ችግር ለመቋቋም ይረዳሃል።—ኢሳይያስ 65:17
ከልክ በላይ አትጨነቅ
በሚከተሉት ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ የወጡትን ጽሑፎች ማንበብህ ብቻህን መሆንህ የሚያስከትልብህን ውጥረት ለመቋቋምና ‘መጨነቅህን ለመተው’ ይረዳሃል።—ማቴዎስ 6:25
ከጓደኞችህ ጋር አዘውትረህ ተነጋገር
ጓደኝነት ለአእምሯዊም ሆነ ለስሜታዊ ጤንነትህ ጠቃሚ ነው፤ በተለይ በአካል ሰዎችን ማግኘት በማይቻልበት ጊዜ ጓደኝነት ይበልጥ አስፈላጊ ነው። ከቤት መውጣት የማትችል ከሆነ በቪዲዮ ኮንፈረንስ ወይም በስልክ አማካኝነት ከጓደኞችህ ጋር ያለህን ዝምድና ማጠናከርና አዳዲስ ጓደኞች ማፍራት ትችላለህ። የሚከተሉት ርዕሶች “እውነተኛ ወዳጅ” ለማግኘት እንዲሁም ጥሩ ጓደኛ ለመሆን ይረዱሃል።—ምሳሌ 17:17
አካላዊ እንቅስቃሴ አድርግ
መጽሐፍ ቅዱስ ‘የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንደሚጠቅም’ ይናገራል። (1 ጢሞቴዎስ 4:8) በተለይ ብቻህን በምትሆንበት ጊዜ የአእምሮ ጤንነትህን ለመጠበቅና ደስተኛ ለመሆን ይረዳሃል። ከቤት መውጣት በማትችልበት ጊዜም ጭምር አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ የምትችልበት መንገድ ይኖራል።