በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

TheCrimsonMonkey/E+ via Getty Images

አካባቢያዊ ችግሮች—የአምላክ መንግሥት ምን እርምጃ ይወስዳል?

አካባቢያዊ ችግሮች—የአምላክ መንግሥት ምን እርምጃ ይወስዳል?

 “የአየር ንብረት አደጋ በሰዎች፣ በከተሞችና በሥነ ምህዳሩ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ ነው። በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት እያየሉ የመጡት አውዳሚ አውሎ ነፋሶች በዓለም ዙሪያ መኖሪያ ቤቶችን እያወደሙ ነው፤ ብዙዎችንም መተዳደሪያ እያሳጡ ነው። የውቅያኖሶች ሙቀት እየጨመረ በመሆኑ በውስጣቸው የሚኖሩ ዝርያዎች የመጥፋት አደጋ ተጋርጦባቸዋል።”—ኢንገር አንደርሰን እንደተናገሩት፣ በምክትል ዋና ጸሐፊ ማዕረግ የተመድ የአካባቢ ጥበቃ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር፣ ሐምሌ 25, 2023

 መንግሥታት ለዚህ ዓለም አቀፍ ችግር እልባት ለመስጠት ተባብረው ይሠሩ ይሆን? ዘላቂ መፍትሔ ማግኘትስ ይችላሉ?

 መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው የምድርን አካባቢያዊ ችግሮች ሙሉ በሙሉ መፍታት የሚችል ደግሞም ይህን የሚያደርግ መንግሥት አለ። “የሰማይ አምላክ . . . መንግሥት ያቋቁማል” በማለት መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፤ ይህ መንግሥት መላዋን ምድር ያስተዳድራል። (ዳንኤል 2:44) ይህ ዓለም አቀፍ መንግሥት በሚገዛበት ወቅት ሰዎች እርስ በርሳቸውም ይሁን በምድር ላይ “ምንም ዓይነት ጉዳት ወይም ጥፋት አያደርሱም።”—ኢሳይያስ 11:9