በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

Kim Steele/The Image Bank via Getty Images

የኢኮኖሚ ቀውስ—የአምላክ መንግሥት ምን እርምጃ ይወስዳል?

የኢኮኖሚ ቀውስ—የአምላክ መንግሥት ምን እርምጃ ይወስዳል?

 በዓለም ዙሪያ ያሉ በርካታ ሰዎች ለኑሮ የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች ማግኘት ከጊዜ ወደ ጊዜ ፈታኝ እየሆነባቸው ነው።

  •   በቅርቡ የወጣ አንድ ዓለም አቀፋዊ ሪፖርት a እንደገለጸው “ሰዎች በወር ውስጥ የሚያገኙት ደሞዝ ያለው የመግዛት አቅም አስደንጋጭ በሆነ መጠን ቀንሷል።” አክሎም ሪፖርቱ፣ ምንም እርምጃ ካልተወሰደ “የኑሮ ልዩነት እንደሚጨምር” እንዲሁም “የአብዛኞቹ ሠራተኞችና የቤተሰቦቻቸው የኑሮ ደረጃ” እንደሚቀንስ አስጠንቅቋል።

 መንግሥታት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ለሄደው ለዚህ የኢኮኖሚ ቀውስ መፍትሔ ማበጀት ቀርቶ በጥቂቱም እንኳ ችግሩን ማስታገስ ይችሉ ይሆን?

 መጽሐፍ ቅዱስ የኑሮ ልዩነትን ጨምሮ ሁሉንም የኢኮኖሚ ችግሮች መፍታት ስለሚችል፣ ደግሞም እንዲህ ስለሚያደርግ አንድ መንግሥት ይናገራል። ‘የሰማይ አምላክ መንግሥት እንደሚያቋቁም’ ማለትም መላዋን ምድር የሚያስተዳድር አንድ አገዛዝ እንደሚመሠርት ይገልጻል። (ዳንኤል 2:44) በዚህ ዓለም አቀፋዊ አገዛዝ ሥር፣ የሚረሳ ወይም ችላ የሚባል አንድም ሰው አይኖርም። (መዝሙር 9:18) የአምላክ መንግሥት፣ ተገዢዎቹ ደስተኛ ለመሆን የሚያስፈልጓቸው ነገሮች በሙሉ እንዲሟሉላቸው ያደርጋል። ሁሉም ሰው የድካሙን ውጤት ማጣጣም ይችላል።—ኢሳይያስ 65:21, 22

a የዓለም የሥራ ድርጅት ዓለም አቀፍ የደሞዝ ሪፖርት ከ2022-23