በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

hadynyah/E+ via Getty Images

ነቅታችሁ ጠብቁ!

ጦርነትንና የአየር ንብረት ለውጥን ተከትሎ የመጣው ዓለም አቀፍ የምግብ እጥረት—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ጦርነትንና የአየር ንብረት ለውጥን ተከትሎ የመጣው ዓለም አቀፍ የምግብ እጥረት—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 የዩክሬን ጦርነት የአየር ንብረቱ ለውጥ ካስከተለው መዘዝ ጋር ተዳምሮ ዓለም አቀፉን የምግብ አቅርቦት እያቃወሰው ይገኛል። በተለይ ብዙዎች በቂ ምግብ ለማግኘት በሚቸገሩባቸው በማደግ ላይ ባሉ አገራት ውስጥ ይህ ችግር ይበልጥ አሳሳቢ ሆኗል።

  •   “ጦርነት፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የነዳጅ ዋጋ መናርና እነዚህን የመሳሰሉ ሌሎች ምክንያቶች የምግብ ምርትና አቅርቦት እንዲቃወስ አድርገዋል።”—አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ፣ ሐምሌ 17, 2023

  •   “ባለሙያዎች ሩሲያ የእህል አቅርቦት ስምምነቱን ማቋረጧ በዓለም ዙሪያ የተከሰተውን የምግብ እጥረት እንደሚያባብሰውና በተለይ በሰሜን አፍሪካና በመካከለኛው ምሥራቅ ባሉ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው አገሮች የምግብ ዋጋ የባሰ እንዲጨምር እንደሚያደርግ ተንብየዋል።”—Atalayar.com፣ ሐምሌ 23, 2023

 መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ምግብ እጥረትና ስለ ወደፊቱ ጊዜ ምን እንደሚል ተመልከት።

መጽሐፍ ቅዱስ የምግብ እጥረት እንደሚከሰት አስቀድሞ ተናግሯል

  •   ኢየሱስ “ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሳል። . . . የምግብ እጥረት . . . ይከሰታል” በማለት ተንብዮአል።—ማቴዎስ 24:7

  •   የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የሆነው የራእይ መጽሐፍ ስለ አራት ምሳሌያዊ ፈረሰኞች ይናገራል። ከእነዚህ ፈረሰኞች መካከል አንዱ ጦርነትን ይወክላል። ረሃብን የሚወክል ሌላ ፈረሰኛ ይህን ፈረሰኛ ይከተለዋል፤ የዚህ ፈረሰኛ ግልቢያ ምግብ በአነስተኛ መጠን የሚከፋፈልበትንና እጅግ ከፍተኛ በሆነ ዋጋ የሚሸጥበትን ጊዜ ያመለክታል። ጥቅሱ እንዲህ ይላል፦ “ጥቁር ፈረስ ቆሞ አየሁ፤ ተቀምጦበት የነበረውም በእጁ ሚዛን ይዞ ነበር። ከዚያም . . . ‘አንድ እርቦ ስንዴ ለአንድ ቀን ደመወዝ፤ ሦስት እርቦ ገብስም ለአንድ ቀን ደመወዝ ይሁን’ . . . የሚል ድምፅ ሰማሁ።”—ራእይ 6:5, 6 አዲሱ መደበኛ ትርጉም

 ስለ ምግብ እጥረት የሚናገሩት እነዚህ ትንቢቶች መጽሐፍ ቅዱስ ‘የመጨረሻዎቹ ቀናት’ በማለት በሚጠራው በአሁኑ ጊዜ ፍጻሜያቸውን እያገኙ ነው። (2 ጢሞቴዎስ 3:1) ስለ “መጨረሻዎቹ ቀናት” እና በራእይ መጽሐፍ ላይ ስለተጠቀሱት አራት ፈረሰኞች ግልቢያ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከ1914 ወዲህ የዓለም ሁኔታ ተቀይሯል የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት እንዲሁም “አራቱ ፈረሰኞች—እነማን ናቸው?” የሚለውን ርዕስ አንብብ።

መጽሐፍ ቅዱስ ምን መፍትሔ ይዟል?

  •   መጽሐፍ ቅዱስ የምግብ ዋጋ መናርንና የምግብ እጥረትን ጨምሮ የተለያዩ ተፈታታኝ ሁኔታዎችን ለመቋቋም የሚረዳ ጠቃሚ ምክር ይዟል።በአነስተኛ ገቢ መኖር የምትችለው እንዴት ነው?” በሚለው ርዕስ ላይ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጣቸውን አንዳንድ ምክሮች ማየት ትችላለህ።

  •   መጽሐፍ ቅዱስ ወደፊት የተሻለ ጊዜ እንደሚመጣም ተስፋ ይሰጠናል። ወደፊት ‘በምድር ላይ እህል እንደሚትረፈረፍና’ ሁሉም ሰው በቂ ምግብ እንደሚያገኝ ይናገራል። (መዝሙር 72:16) ስለዚህ ተስፋ ይበልጥ ለማወቅና በዚህ ተስፋ ላይ እምነት መጣል የምትችለው ለምን እንደሆነ ለመረዳት “የተሻለ ጊዜ ይመጣል ብለን ተስፋ ማድረግ እንችላለን?” የሚለውን ርዕስ አንብብ።