በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

Rui Almeida Fotografia/Moment via Getty Images

ነቅታችሁ ጠብቁ!

ፖለቲካዊ ዓመፅ—⁠መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ፖለቲካዊ ዓመፅ—⁠መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 በተለያዩ ቦታዎች እየተከሰተ ያለው ፖለቲካዊ ዓመፅ ዓለምን እያናወጣት ነው።

  •   ሜክሲኮ ውስጥ ምርጫ እየተካሄደ ባለበት ከ2023-2024 ባለው ጊዜ ውስጥ 39 የፖለቲካ ዕጩዎች የተገደሉ ከመሆኑም ሌላ ከዚህ በፊት ታይቶ በማያውቅ መጠን ፖለቲካዊ ዓመፅ በተለያዩ መንገዶች እየተከሰተ ነው።

  •   ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አውሮፓ ውስጥ ፖለቲካዊ ዓመፅ የሚንጸባረቅባቸው በርካታ ድርጊቶች ተፈጽመዋል፤ ግንቦት 15, 2024 በስሎቫኪያ ጠቅላይ ሚኒስትር ላይ የተፈጸመው የግድያ ሙከራ ከእነዚህ መካከል አንዱ ነው።

  •   ሐምሌ 13, 2024 በዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ የተፈጸመው የግድያ ሙከራ የአገሪቱን ሕዝብ አስደንግጧል።

 ፖለቲካዊ ዓመፅ ይህን ያህል የተስፋፋው ለምንድን ነው? የሚያበቃበት ጊዜ ይመጣ ይሆን? መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ፖለቲካዊ ክፍፍል እንደሚኖር ትንቢት ተነግሯል

 መጽሐፍ ቅዱስ በምንኖርበት ዘመን ማለትም “በመጨረሻዎቹ ቀናት” ብዙ ሰዎች ለዓመፅና ለግጭት የሚዳርጉ ባሕርያትን እንደሚያንጸባርቁ ትንቢት ተናግሯል።

  •   “በመጨረሻዎቹ ቀናት ለመቋቋም የሚያስቸግር በዓይነቱ ልዩ የሆነ ዘመን እንደሚመጣ ይህን እወቅ። ምክንያቱም ሰዎች . . . የማያመሰግኑ፣ ታማኝ ያልሆኑ፣ . . . ለመስማማት ፈቃደኞች ያልሆኑ፣ . . . ጨካኞች፣ . . . ከዳተኞች፣ ግትሮች፣ በኩራት የተወጠሩ . . . ይሆናሉ።”​—2 ጢሞቴዎስ 3:1-4

 በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ በዘመናችን ፖለቲካዊ ዓመፅና ብጥብጥ እንደሚኖር ይናገራል። (ሉቃስ 21:9 ግርጌ) ያም ቢሆን፣ ፖለቲካዊ ዓመፅና ክፍፍል የሚያበቃበት ጊዜ ይመጣል።

ፖለቲካዊ ዓመፅ የሚያበቃበት ጊዜ

 አምላክ ሰብዓዊ መንግሥታትን በሙሉ አጥፍቶ በሰማይ ላይ ባቋቋመው መንግሥት እንደሚተካቸው መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።

  •   “የሰማይ አምላክ ፈጽሞ የማይጠፋ መንግሥት ያቋቁማል። ይህም መንግሥት [ሌሎቹን] መንግሥታት ሁሉ ያደቅቃል፤ ፈጽሞም ያጠፋቸዋል፤ እሱም ብቻውን ለዘላለም ይቆማል።”​—ዳንኤል 2:44

 የአምላክ መንግሥት በዓለም ዙሪያ እውነተኛ አንድነትና ሰላም ያሰፍናል።

  •   የመንግሥቱ ገዢ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ “የሰላም መስፍን” ተብሎ ተጠርቷል፤ እንዲሁም “ሰላሙ ፍጻሜ አይኖረውም።”​—ኢሳይያስ 9:6, 7

  •   አሁንም እንኳ የመንግሥቱ ተገዢዎች በሰላም መኖር የሚቻልበትን መንገድ እየተማሩ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ይህ የሚያስገኘውን ውጤት ሲናገር እንዲህ ይላል፦ “ሰይፋቸውን ማረሻ፣ ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ። አንዱ ብሔር በሌላው ብሔር ላይ ሰይፍ አያነሳም፤ ከእንግዲህ ወዲህ ጦርነት አይማሩም።”​—ኢሳይያስ 2:3, 4

 ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት “የአምላክ መንግሥት ወደፊት ምን ያከናውናል?” የሚለውን ርዕስ አንብብ፤ እንዲሁም የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው? የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት።