በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

JenkoAtaman/stock.adobe.com

ነቅታችሁ ጠብቁ!

2023 የተስፋ ዓመት ይሆን?—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

2023 የተስፋ ዓመት ይሆን?—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 ዓመተ 2023⁠ን “ሀ” ብለን ጀምረናል፤ ሁላችንም ለራሳችንም ሆነ ለቤተሰቦቻችን መልካሙን እንመኛለን። ይሁንና በዚህ ዓመት ቸር ይገጥመናል ብለን ተስፋ ለማድረግ ምክንያት አለን?

መጽሐፍ ቅዱስ ተስፋ ይሰጣል

 መጽሐፍ ቅዱስ ምሥራች ያበስረናል፤ ዛሬ ያሉብን ችግሮች ጊዜያዊ እንደሆኑና በቅርቡ እልባት እንደሚያገኙ ይነግረናል። እንዲያውም መጽሐፍ ቅዱስ ለእኛ የተጻፈው “ከቅዱሳን መጻሕፍት በምናገኘው መጽናኛ ተስፋ ይኖረን ዘንድ” ነው።—ሮም 15:4

ለዛሬም ስንቅ የሚሆንህ ተስፋ

 የመጽሐፍ ቅዱስ ተስፋ “ለሕይወታችን እንደ መልሕቅ” ነው። (ዕብራውያን 6:19 የግርጌ ማስታወሻ) ይህ ተስፋ የሕይወት ማዕበል ሲበረታ እንዳንናወጥ ይረዳናል። ዛሬ የሚገጥሙንን ችግሮች ችለን እንድናልፍ፣ አዎንታዊ አመለካከት እንዲኖረን እንዲሁም ሁልጊዜም ደስተኛ እንድንሆን ያስችለናል። እስቲ የሚከተሉትን ምሳሌዎች ተመልከት፦

ተስፋህን አለምልም

 ቸር ቢገጥመን ብለው ተስፋ የሚያደርጉ ብዙዎች ናቸው፤ ሆኖም ተስፋቸው ይፈጸም አይፈጸም እርግጠኛ መሆን አይችሉም። የመጽሐፍ ቅዱስ ተስፋ ግን የሕልም እንጀራ አይደለም። ለምን? ምክንያቱም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ ተስፋዎችን የሰጠው ይሖዋ አምላክ a ራሱ ነው፤ እሱ ደግሞ “ሊዋሽ [የማይችል] አምላክ” ነው። (ቲቶ 1:2) የሰጣቸውን ተስፋዎች በሙሉ ለመፈጸም አቅሙ ያለው ይሖዋ ብቻ ነው፤ እሱ “ደስ ያሰኘውን ነገር ሁሉ ያደርጋል።”—መዝሙር 135:5, 6

 መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሚገኘው አስተማማኝ ተስፋ ሕይወትህን እንድታለመልም ሞቅ ያለ ግብዣ እናቀርብልሃለን። “ቅዱሳን መጻሕፍትን በሚገባ በመመርመር” በዚህ ተስፋ ለመተማመን አጥጋቢ ምክንያት ማግኘት ትችላለህ። (የሐዋርያት ሥራ 17:11) ለዚህ እንዲያግዝህ በማሰብ በአስተማሪ መጽሐፍ ቅዱስን በነፃ የምትማርበት ዝግጅት አድርገናል፤ ይህን ኮርስ ለምን አትሞክረውም? አዲሱን የ2023 ዓመት በተስፋ እንድትጀምር እንመኝልሃለን!

a ይሖዋ የአምላክ የግል ስም ነው።—መዝሙር 83:18