በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር | በአገልግሎት የምታገኙትን ደስታ አሳድጉ
የሰዎችን ልብ መንካት
አምላክን መታዘዝ የሚመነጨው ከልብ ነው። (ምሳሌ 3:1) በመሆኑም በምናስተምርበት ወቅት የሚሰሙንን ሰዎች ልብ ለመንካት ጥረት ማድረግ ይኖርብናል። ታዲያ ይህን ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?
ለጥናታችሁ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነቶች በማስተማር ብቻ አትወሰኑ፤ እነዚህን እውነቶች ከራሱ ሕይወት እንዲሁም ከይሖዋ ጋር ካለው ዝምድና ጋር እንዲያዛምድ እርዱት። የመጽሐፍ ቅዱስ መሥፈርቶች የአምላክን ፍቅር፣ ጥሩነትና ጽድቅ የሚያሳዩት እንዴት እንደሆነ እንዲገነዘብ እርዱት። ስለሚማረው ነገር ያለውን ስሜት እንዲያጤን ለመርዳት በዘዴ ጥያቄዎች ጠይቁት። ያለውን የተሳሳተ አመለካከት ወይም ልማድ ማስተካከሉ ስለሚያስገኝለት ጥቅም እንዲያመዛዝን እርዱት። ጥናታችሁ ለይሖዋ ያለው ልባዊ ፍቅር እንዳደገ ስትመለከቱ በአገልግሎት የምታገኙት ደስታ ይጨምራል።
ደቀ መዛሙርት የማድረጉ ሥራ የሚያስገኘውን ደስታ አጣጥሙ—ክህሎታችሁን አሻሽሉ—የሰዎችን ልብ መንካት የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
-
ኒታ ጄድን “ሰኞ ባወራነው ነገር ላይ አሰብሽበት?” ብላ የጠየቀቻት ለምንድን ነው?
-
ጄድ የመጽሐፍ ቅዱስ መሥፈርቶች ይሖዋ ለእሷ ያለውን ፍቅር እንደሚያሳዩ እንድትገነዘብ ኒታ የረዳቻት እንዴት ነው?
-
ጄድ ለአምላክ ያላትን ፍቅር ማሳየት የምትችልበትን መንገድ እንድታመዛዝን ኒታ የረዳቻት እንዴት ነው?