በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ደፋር መሆን ያን ያህል ከባድ አይደለም

ደፋር መሆን ያን ያህል ከባድ አይደለም

ድፍረት ጠንካራ፣ የማይበገርና ልበ ሙሉ መሆንን የሚያመለክት ባሕርይ ነው። ደፋር ሰው ፍርሃት የሚባል ነገር አይሰማውም ማለት አይደለም። ከዚህ ይልቅ ፍርሃት ቢሰማውም ትክክለኛውን እርምጃ ከመውሰድ ወደኋላ አይልም። የእውነተኛ ድፍረት ምንጭ ይሖዋ ነው። (መዝ 28:7) ወጣቶች ደፋር እንደሆኑ ማሳየት የሚችሉት እንዴት ነው?

የፈሪዎችን ሳይሆን የደፋሮችን አርዓያ ተከተሉ! የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ወጣቶች ድፍረት የሚጠይቁ ምን ሁኔታዎች ያጋጥሟቸዋል?

  • ደፋር እንድንሆን የሚረዱን የትኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባዎች ናቸው?

  • ድፍረት ማሳየት እኛንም ሆነ የሚመለከቱንን ሰዎች የሚጠቅመው እንዴት ነው?