በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

አሮጊቶችን እንደ እናቶች፣ ወጣት ሴቶችን ደግሞ እንደ እህቶች አድርጋችሁ ያዙ

አሮጊቶችን እንደ እናቶች፣ ወጣት ሴቶችን ደግሞ እንደ እህቶች አድርጋችሁ ያዙ

ቅዱሳን መጻሕፍት እንደሚመክሩን በዕድሜ የገፉ ክርስቲያኖችን እንደ እናት ወይም እንደ አባት፣ ወጣቶችን ደግሞ እንደ ወንድም ወይም እንደ እህት አድርገን መያዝ ይኖርብናል። (1 ጢሞቴዎስ 5:1, 2ን አንብብ።) በተለይ ወንድሞች፣ እህቶችን በአክብሮት መያዝ ይኖርባቸዋል።

አንድ ወንድም አንዲት እህትን አያሽኮረምምም፤ እንዲሁም ከእሱ ጋር ስትሆን እንዲጨንቃት የሚያደርግ ምንም ነገር አያደርግም። (ኢዮብ 31:1) አንድ ያላገባ ወንድም የፍቅር ግንኙነት የመጀመር ሐሳብ ሳይኖረው እንደዚያ ዓይነት መልእክት የሚያስተላልፍ ነገር በማድረግ በአንዲት ነጠላ እህት ስሜት አይጫወትም።

እህቶች በአክብሮት ጥያቄ ሲያነሱ፣ ሌላው ቀርቶ ትኩረት የሚያሻው ነገር እንዳለ ሲጠቁሙ ሽማግሌዎች፣ እህቶች የሰጡትን ሐሳብ በቁም ነገር ይመለከቱታል። ሽማግሌዎች፣ ከለላ የሚሆናቸው ባል ለሌላቸው እህቶች ለየት ያለ አሳቢነት ያሳያሉ።—ሩት 2:8, 9

ለዘላለም የሚኖረውን ፍቅር በጉባኤ ውስጥ አሳዩ—ለመበለቶች እና አባት ለሌላቸው ልጆች የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ጉባኤው ለእህት ምዪንት ለየት ያለ ፍቅር ያሳየው እንዴት ነው?

  • ጉባኤው ያሳየው ፍቅር በአካባቢው ለሚኖሩ ሰዎች ጥሩ ምሥክርነት የሰጠው እንዴት ነው?

  • ጉባኤው ያሳየው ፍቅር በእህት ምዪንት ልጆች ላይ ምን በጎ ተጽዕኖ አሳድሯል?

በጉባኤህ ላሉ እህቶች ፍቅርና አሳቢነት ማሳየት የምትችልባቸው አንዳንድ መንገዶች የትኞቹ ናቸው?