ክርስቲያናዊ ሕይወት
የውይይት ናሙናዎችን መጠቀም የምንችለው እንዴት ነው?
የውይይት ናሙናዎች የሚዘጋጁት በደንብ ታስቦባቸው ነው፤ ደግሞም በርካታ አስፋፊዎች የውይይት ናሙናዎቹን በክልላቸው ውስጥ ውጤታማ ሆነው አግኝተዋቸዋል። ሆኖም በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ያለው ሁኔታ ስለሚለያይ አስፋፊዎች በአገልግሎታቸው ላይ በክልላቸው ውስጥ ያሉትን ሰዎች የሚማርክ የተለየ አቀራረብ መጠቀም ወይም የተለየ ርዕሰ ጉዳይ ማንሳት ይችላሉ። እርግጥ ነው፣ በልዩ ዘመቻዎች ወቅት ሁላችንም የተሰጠንን መመሪያ መከተል ይኖርብናል። ግባችን ኢየሱስ የመንግሥቱን ምሥራች እንድንሰብክ የሰጠንን ተልዕኮ መፈጸም ነው።—ማቴ 24:14
አስፋፊዎች የተማሪ ክፍል ሲያቀርቡ በክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ ላይ ባለው የውይይት ናሙና ላይ የቀረበውን ርዕሰ ጉዳይ መጠቀም አለባቸው። (ለምሳሌ ለሐምሌ እና ለነሐሴ የቀረበው ርዕሰ ጉዳይ ‘አምላክ ለሰው ልጆች ያለው ዓላማ’ ነው።) ሆኖም የተለየ መመሪያ ካልተሰጠ በቀር በክልላቸው ውጤታማ የሆነ ሌላ ጥያቄ፣ ጥቅስ፣ ለቀጣዩ ጊዜ የሚሆን ጥያቄ ወይም መቼት መምረጥ ይችላሉ። ይህ ሐሳብ በሰኔ 2020 የስብሰባ አስተዋጽኦ ገጽ 8 ላይ በወጣው መመሪያ ላይ የተደረገ ማስተካከያ ነው።