ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
የምትሰጡት ነገር መሥዋዕት ነው?
ዳዊት በአረውና አውድማ ላይ መሠዊያ እንዲሠራ ታዘዘ (2ሳሙ 24:18)
አረውና መሬቱንና መሥዋዕት ሆነው የሚቀርቡትን እንስሳት በነፃ ለመስጠት ፈቃደኛ ነበር (2ሳሙ 24:21-23)
ዳዊት ምንም ያልከፈለበትን ነገር መሥዋዕት አድርጎ ለማቅረብ ፈቃደኛ አልሆነም (2ሳሙ 24:24, 25፤ it-1 146)
ይሖዋ ከመንግሥቱ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ለማራመድ ስንል ጊዜያችንን፣ ጉልበታችንንና ገንዘባችንን በፈቃደኝነት መሥዋዕት ስናደርግ ይደሰታል። (w12 1/15 18 አን. 8) ለይሖዋ የምታቀርበውን “የውዳሴ መሥዋዕት” ለመጨመር የትኞቹን ግቦች ማውጣት ትችላለህ?—ዕብ 13:15