ክርስቲያናዊ ሕይወት
‘ለምሥራቹ መሟገትና በሕግ የጸና እንዲሆን ማድረግ’
እስራኤላውያን ቤተ መቅደሱን መልሰው እንዳይገነቡ ተቃዋሚዎች ጥረት ባደረጉበት ወቅት አይሁዳውያኑ ሥራውን ለማስቀጠል የሚያስችል ሕጋዊ ፈቃድ ለማግኘት ጥረት አድርገዋል። (ዕዝራ 5:11-16) ክርስቲያኖችም በተመሳሳይ ለምሥራቹ ለመሟገትና በሕግ የጸና እንዲሆን ለማድረግ ጥረት ያደርጋሉ። (ፊልጵ 1:7) ለዚህም ሲባል በ1936 በዋናው መሥሪያ ቤት የሕግ ክፍል ተቋቁሟል። በዛሬው ጊዜ፣ በዋናው መሥሪያ ቤት ያለው የሕግ ክፍል በዓለም ዙሪያ ለመንግሥቱ ጉዳዮች ጥብቅና ይቆማል። የሕግ ክፍሉ የመንግሥቱን ጉዳዮች ያራመደውና ለአምላክ ሕዝቦች ጥቅም ያስገኘው እንዴት ነው?
በዋናው መሥሪያ ቤት ያለው የሕግ ክፍል የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
-
የይሖዋ ምሥክሮች ከሕግ ጋር በተያያዘ የትኞቹ ችግሮች ያጋጥሟቸዋል?
-
የትኞቹን የሕግ ድሎች አግኝተናል? ምሳሌ ስጥ
-
እያንዳንዳችን ‘ለምሥራቹ በመሟገትና በሕግ የጸና እንዲሆን በማድረግ’ ረገድ ምን ሚና መጫወት እንችላለን?
-
ከአምላክ ሕዝቦች ጋር የተያያዙ ሕግ ነክ ጉዳዮችንና በእምነታቸው ምክንያት የታሰሩ የይሖዋ ምሥክሮችን ዝርዝር ድረ ገጻችን ላይ ማግኘት የምንችለው እንዴት ነው?